ግልጽ ያጨረታ ማስታወቂያ 

የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ለ2012 በጀት ዓመት ለተለያዩ ሞዴል ተሸከርካሪዎች የተለያዩ ጎማዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡ 

 • ተጫራቶች በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የእቅራቢነት የምዝገባ ወረቀት ያላቸው፡፡ 
 • የጨረታው ዶክመንት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመከፈል ድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ከግዥ ፋይናንስና ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በጥሬ ገንዘብ በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ 
 • የጨረታ ሰነድ በውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ቢሮ ቁጥር 05 ከ1፡30 እስከ 11:30 ዘወትር በስራ ሰዓትና ቀን መግዛትና ማስገባት ይቻላል፡፡ 
 • ጨረታው በማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በ3፡00 የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በተመሣሣይ ቀን 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ 
 • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ዶክመንቱ ሲከፈት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ 
 • የጨረታው ዶክመንት በታሸገ ፖስታ የእያንዳንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት በተጨማሪ በጨረታ ዶከመንቱ ውስጥ የተዘጋጁት ፎርማት ተሞልተውና ተፈርመው መቅረብ አለባቸው፡፡ 
 • ያሸነፈው ተጫራች የተጠየቀውን እቃ የግዥ ትዕዛዝ እንደተሰጠው በእስፔስፊኬሽኑ እና ስናሙናው መሠረት በ45 ቀናት ውስጥ በድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን በሚገኝበት መጋዘን አቅርቦ ማስረከብ አለበት፡፡ 
 • በዶክመንቱ ከተሰጠው ስፔስፊኬሽን ወይም ሳምፕል ወጪ የሚቀርብ ተቀባይነት የለውም፡፡ 
 • የጨረታው አሸናፊ ካሸነፈው ዋጋ 10% ውል ማስከበሪያ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ያልተገደበ የባንክ ጋራንቲ ማሰያዝ የሚችል፡፡ 
 • በጨረታ ሂደት ጨረታውን ለማዛባት ለማጭበርበር የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆንና በመንግሥት ግዥ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡ 
 • የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ዶክመንት ተቀባይነት የለውም፡፡ 
 • ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠየቀ ነው:: 
 • አድራሻ፡- ድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ቀበሌ 03 
 • ድሬዳዋ ስልክ ቁጥር፡- 025 112 48 92 ፖሣቁ. 446 

የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና 

ፍሣሽ ባስሥልጣን