የጨረታ ማስታወቂያ 

የአራዳ ክ/ከተማ የወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ በ2012 በጀት ዓመት የ2ኛ ዙር አገልግሎት የሚውሉ

 • የፅህፈት መሳሪያዎች፤
 • የፅዳት እቃዎች፤
 • የደንብ ልብሶች
 • ህትመቶች፣ አላቂ የህከምና እቃዎች፤
 • ቋሚ የህክምና እቃዎች እና
 • የተለያዩ ቋሚ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እና ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው። 
 1.  በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የገበረ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆነ። 
 2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር የአቅራቢነት ምዝገባ ያደረገ።
 3. ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር ሰነዱን ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ 4ተኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ። ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው እለት 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። 
 4.  ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች ወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ ንብረት ከፍል ሙሉ ወጪውን ችለው ማስረክብ አለባቸው:: 
 5. የጨረታ ማስረከቢያ ብር 2% ከባንክ በተመሰከረ ቼክ በጥሬ ገንዘብ ወይም በCPO ማስያዝ አለባቸው:: ሙሉ ዝርዝር መረጃው ከሰነዱ ላይ መመልከት አለባቸው።
 6. ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው። 
 7. ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም:: 
 8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው :: 
 9. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ እለባቸው::
 10. ተጫራቾች በሰም የታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው:: አድራሻ፡- በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ ከሰሜን ሆቴል ጀርባ ሲሲኤፍ ግቢ አጠገብ:: መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011 126 52 92 /011 111 96 29 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ። 

በአራዳ ክፍስ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ