የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 004/2012 

የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ፑል የመንግስት ግዥ ቡድን በግልጽ ጨረታ በፑሉ ተጠቃሚ ለሆኑ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት ቋሚና አላቂ እቃዎች ግዥዎችን በ7+ምድብ ከፍሎ በግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ 

 • ሎት 1.የኤሌክትሮኒክስ፣ 
 • ሎት 2.የአዳራሽ ሳውንድ ሲስተም፣ 
 • ሎት 3.ቋሚ ዕቃ ፈርኒቸር፣ 
 • ሎት 4.የሻይ ማፊያ ማሽን፣ 
 • ሎት 5.የስፖርት ትጥቅ፣ 
 • ሎት 6.የድንኳን ግዢ፣ 
 • ሎት7.ደንብ ልብስ፣ 
 1. ተጫራቶች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ፣ ቲን ሰርተፍኬት ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 
 2. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች ዋናውንና ኮፒውን በማቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡ 
 3. የጨረታ ሰነዱ በኢንቨሎፕ ታሽጎ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዋናውንና ኮፒውን የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ፑል የመንግስት ግዥ ቡድን 3ኛ ፎቅ ማስገባት ይኖርበታል፡፡ 
 4. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30- 6፡30 ሠዓት ሰነዱ ተመላሽ ተደርጎ በዚህ ቀን ከሠዓት በኋላ በ8፡00 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 
 5. ተጫራቶች በጋዜጣው ላይ በተገለጹት የጨረታ ዓይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡ 
 6. ተጫራቶች ሙሉ ስማቸውን አድራሻቸውንና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ በመፈረም ማቅረብና ማረጋገጥ አለባቸው፡፡ 
 7. የጨረታ ማስከበሪያ ከሎት 1 እስከ 6 5,000 ብር ሎት 7 ብቻ 2,000 ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO በኮልፌ ቀራንዮ ከፍለ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ፑል የመንግስት ግዥ ቡድን ስም ተሰርቶ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ 
 8. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጨረታ የጨረታ ዓይነቶች ውስጥ የተዘረዘሩትን ያንዱ ዋጋ እና የጠቅላላውን ዋጋ በግልጽ ከጽ/ቤት ገዝተው በወሰዱት ሰነድ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡ 
 9. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው ስፔስፊኬሽን መሰረት ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ 
 10. 1መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆኖ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
 • አድራሻ ኮ/ቀራኒዮ ክፍስ ከተማ ወረዳ 06 የሚገኘው የክፍለ ከተማው ህንፃ 3ኛ ፎቅ ስልክ ቁጥር 0118350897 

የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር 

የኮንስትራክሽን ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ 

ፅ/ቤት የመንግሥት ግዥ ቡድን