በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ 

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ግቢ ለ2012 በጀት ዓመት የሰራተኞች የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የሚያሟሉ አቅራቢዎች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡ 

 1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው 
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው 
 3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ 
 4. ተጫራቶች የግብር ግዴታ መወጣታቸውን እና በመንግስት ጨረታ መካፈል እንደሚችሉ የሚገልጽ የሀገር ውስጥ ገቢ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 5. በፌዴራል ግዥ ኤጀንሲ ድረ ገጽ(www.ppa.gov.et ) በአቅራቢነት የተመዘገበ 
 6. ተጫራቾች የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገቡበትን ቅጽ ፈርመውና ማህተም አድርገው ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 7. የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ ሲፒኦ ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብር 30,000/ሰላሳ ሺህ ብር ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበር የተደራጁ ከሆነ ከአደራጁ መ/ቤት በተጠቀሰው ብር ልክ የጨረታ ማስከበሪያ ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 8. የጨረታ ሰነዱን ከሚዛን ዋናው ግቢ ግዥ ቡድን ቢሮ ፡ ቴፒ ግቢ ግዥ ቡድን ቢሮ እና አዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አሜሪካ ኤምባሲ ፊትለፊት የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ ድርጅት ግቢ ውስጥ ከሚገኘው በዩኒቨርሲቲው ጉዳይ ማስፈፀሚያ ቢሮ በማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/መግዛት ይችላል፡፡ 
 9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉበት 15 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀን 1-30 ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ 
 10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በማሸግ እንዲሁም ፋይናሽያል ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በማሸግ CPOን ጨምሮ ሁሉንም ፖስታዎች በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ አዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አሜሪካ ኤምባሲ ፊትለፊት የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ ድርጅት ግቢ ውስጥ በሚገኘው በዩኒቨርሲቲው ጉዳይ ማስፈጸሚያ ቢሮ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 
 11. ጨረታው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡ እንዲሁም በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በተገኙበት በአዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አሜሪካ ኤምባሲ ፊትለፊት የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ ድርጅት ግቢ ውስጥ በሚገኘው በዩኒቨርሲቲው ጉዳይ ማስፈጸሚያ ቢሮ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡ 
 • ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
 • ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግም:በስልክ ቁጥር 0475560339 
 • በፋክስ ቁጥር 047-135 11 44 መጠየቅ ይችላሉ:: 

ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቴፒ ግቢ