የጨረታ ማስታወቂያ 

በአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በገፈርሳ ውኃ ማጣሪያ ጣቢያ አካባቢ የሚገኙ የተለያዩ ዝርያ ያላቸውን ዛፎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታ እንዲሳተፋ ይጋብ ዛል። 

  1. ተጫራቾች መገናኛገቢዎችእና ጉምሩክ ዋና መ/ቤት አጠገብ በሚገኘው የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ዋና መ/ቤት ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ በመገኘት የጨረታውን ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ሒሳብ ቁጥር 1000005054277 ገቢ አድርገው ያስገቡበትን ደረሰኝ በማቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፣ 
  2. ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁትን የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ዛፎች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ እስከ መክፈቻ ቀኑ በፊት ያለውን ድረስ በሥራ ሰዓት /ከ2፡30-11፡00/ ባለው ጊዜ ውስጥ ጨረታ ሰነዱን በመያዝ ገፈርሳ የውኃ ማጣሪያ ቅጥር ግቢ ጣቢያ በመገኘት በአካል መመልከት ይችላሉ፣ 
  3. ተጫራቾች ለ30 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማቅረብ ይገባቸዋል፣ 
  4. ከጨረታ መነሻ ዋጋ በታች ሞልቶ ያቀረበ ተጫራች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ይሰረዛል፣ 
  5. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ኣሸናፊ ነታቸው በተገለፀላቸው በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ ሙሉ ክፍያውን መክፈል ይኖርባቸዋል። ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ መከፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለባለሥልጣን መ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ መ/ቤቱ ሌሎች አማራጮችን ይጠቀማል፣ 
  6. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፈበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ዛፎቹን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ቆርጠው የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣ 
  7. የጨረታ ሰነዱን በስሙ ያልገዛ ተጫራች በጨረታው ሊሳተፍ አይችልም፣ 
  8. የተሸጠ ጨረታ ሰነድ ተመላሽ አይደረግም፣ 
  9. ፎቶ ኮፒ በተደረገ የጨረታ ሰነድ የተወዳደረ ተጫራች ከጨረታው እንዲሰረዝ ይደረጋል፣ 

የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ 

ባስሥልጣን