የጨረታ ቁጥር 15/2012 

የሁለተኛ ጊዜ የወጣ 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ የግብ ግብ/ገጠር ፋይናንስና አቅርቦት ዳይሬከቶሬት ከሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት CRGE ፕሮጀከት በጀት ድጋፍ ለተንታ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል

 1. የጤፍ መዝሪያ
 2. Hard held harvester
 3. Plot treaher (የቁም መውቂያ) ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። 

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ያሳውቃል። 

 1. በዘርፉ እና ዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ 
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ የሚችሉ 
 3. የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ 
 4. ተጫራቶች የዕቃው አይነት፣ የአምራቹን ሥም የተመረተበትን ሀገር እና የሞዴል ቁጥር ዝርዝር ሙግለጫው (Specification) መሠረት ካታሎግ (Catalogue) ማቅረብ አለበት። 
 5. ተጫራቶች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። 
 6. የሚገዙ የግብዓት ዓይነትና ዝርዝር ሙግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል። 
 7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት አንድ ብር 25,000.00 ለሎት ሁለት ብር 3,000.00 ሎት ሦስት ብር 6,000.00 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው። 
 8. ተጫራቾች የቴከኒካል እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሁለት በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቶች አንድ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኦርጅናል እና አንድ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግብርና ቢሮ የግብርና ግብአት ገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 18 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል። ለዚህ ጨረታ ቴክኒካል ሰነድ መያዝ አለበት ማለት የዕቃዎቹ ዝርዝር መግለጫ (specification)፣ በዘርፉ እና ዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣ የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የማቅረቢያ ቦታ፣ የማቅረቢያ ጊዜ፣ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ቀን እና ካታሎግ (Catalogue)፣ የፋይናንሻል ሠነድ መያዝ ያለበት የጨረታ ማስከበሪያ ( ሲፒኦ) እና ዋጋ መሙያ ፎርም ሲሆን ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡት ግዥ ፈፃሚው መ/ቤት ባዘጋጀው የዋጋ መሙያ ፎርም መሠረት መሆን አለበት። በራስዎ ፎርም የሚሞሉ ከሆነ የእቃው ሞዴል እና ሌሎች አስፈላጊ መጠይቆች መቀየር የለባቸውም። 
 9. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመከፈል የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 6 ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ መ/ቤቱ ወይም ጽ/ቤቱ በመቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፤ 
 10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግብርና ቢሮ የግብርና ግብአት ገጠር ፋይናንስ አቅርቦት ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 በ16ኛው ቀን 2012 ዓም 4፡30 ሰዓት ይከፈታል። 
 11. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 
 12. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር /8 ድረስ በአካል ወይም በፋክስ ቁጥር 0582208771 በመላክ 
 • በስልክ ቁጥር 0582205849/7048 በመደወል ማግኘት ይችላሉ። 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ 

መንግሥት ግብርና ቢሮ 

ባህር ዳር