የጨረታ ማስታወቂያ 

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅ/ቤት የቀበና ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የፋይናንስና ግዢ ንብረት አስተዳደር በጨረታ ቁጥር የቀ/ጤ/አጠ/ጣቢያ 02/2012 መሰረት በ2012 ዓ.ም የበጀት ዓመት ለጤና ጣቢያው አገልግሎት የሚሰጡ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ 

የጨረታ ግዥ መለያ ቁጥር የቀ/ጤ/አጠ/ጣቢያ 02/2012 

 • ሎት ፡-1. የተለያዩ የቢሮ አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች፣
 • 2. የሠራተኛ የደንብ ልብስ፣ 
 • ሎት 2፡-1. የኤሌክትሪክ እቃዎች እና የጥገና እቃዎች፣ 
 • ሎት 3፡- 1. መድሃኒቶች 
 • 2. የላብራቶሪ ኤጀንቶች፣ 
 • 3 አላቂ የህክምና እቃዎች፣ 
 • ሎት 4 የቢሮ ግንባታ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል

በዚሁ መሰረት ፦ 

 1. በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ማንኛውም ተጫራቶች ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆነ የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል :: 
 2. በጥቃቅንና አነስተኛ በኮንስትራከሽን የተደራጁ ሆነው ደረጃቸው አነስተኛ ብቃትና ታዳጊ መካከለኛ የሆኑ፡፡ 
 3. የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ልማት ቁጥጥር ዘርፍ ተመዝነው የሙያ ምዘና ሰርተፍኬት (coc) ያላቸውና ከተደራጁበት ከፍለ ከተማ ስራ እንደሌላቸው ወይም የሚገለጽ ማስረጃ ማቅረብ፡፡ 
 4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጤና ጣቢያው ቀርበው መግዛት ይችላሉ። 
 5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ 4500 (አራት ሺ አምስት መቶ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ(CPO) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 6. ማንኛውም ተጫራች ሰነድ ለማስገባት በሚመጣበት ጊዜ ላምፕል ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች አብሮ ማስገባት አለበት፡፡ ተጫራቾ የጨረታውን ሰነድ ዋናውን ከ(CPO) ጋር እንዲሁም ከኮፒ ሰነድ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ እና በፊርማ በማረጋገጥ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 – 11፡00 ሰዓት የጤና ጣቢያው የፋይናንስና ግዥ ን/አስተዳደር ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 28 ማስገባት አለባቸው። የጨረታው ሳጥን በ10ኛው የስራ ቀን በ11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በአራዳ ክ/ከተማ ቀበና ጤና አጣቢያ በሰራተኛ ከፍል አዳራሽ ይከፈታል:: ተጫራቾች የሚያቀርቡት የአንዱ ዋጋ ሆነ ጠቅላላ ዋጋ ሲቀመጥ ቫቱን አካቶ መሆን አለበት፡፡ 
 7. ማንኛውም ተወዳዳሪ ተጫራች በተመዘገበበት ንግድ ፈቃድ በዘርፉ ብቻ መወዳደር አለበት:: 
 8. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ ውል ከተፈራረመበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ እስከ ጤና ጣቢው ንብረት ክፍል በራሱ ትራንስፖርት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ 
 9. የጨረታ ሰነድ የገዙትን ኦሪጅናልና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው። 
 10. ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም። 
 11. ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ኦው። 

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-

 • አድርሻ፡-ቀበና ሼል ከመድረሱ በፊት የኦሮሚያ ድን ህንፃ ገባ ብሎ ቀበና ምሥራቅ ፀሐይ መድሃኒያዓለም ቤተክርስቲያን አጠገብ 
 • ስልክ ቁጥር፡- 011 123-56-07/011-812-00-71 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ 

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ፅ/ቤት 

የቀበና ጤና አጠባበቅ ጣቢያ የፋይናንስና ግዢ ንብረት አስተዳደር