ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ግልጽ የጨረታ መለያ ቁጥር 02/2012 

በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በወረዳ 08 የበአታ ጤና ጣቢያ 

 1. ሎት 1፡ መድሃኒት
 2. ሎት 2፡ ደንብ ልብስ
 3. ሎት 3፡ ህትመት 
 4. ሎት 4፡ የጽዳት እቃዎች 
 5. ሎት 5፡ ቋሚ እቃዎች 

በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል ስለዚህ በጨረታ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ መሟላት ይኖርባቸዋል፡፡ 

 1. ተጫራቶች በተሰማሩበት የስራ መስክ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸውና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ 
 2. የመንግስት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
 3. ተጫራቾች የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN )ያለቸው ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ከብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ፡፡
 4. ተጫራቾች በጨረታ ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወደ መ/ቤታችን ግቢ ማድረስ ይኖርባቸዋል ፡፡
 5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል የተጫረቱበትን ዋጋ 2% በድርጅቱ ስም ሲፒኦ በባንክ የተረጋገጠ ከመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 
 6. ተጫራቾች በአንድ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም ፡፡
 7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በጥንቃቄ ሞልተው በመፈረምና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋና ኮፒውን  በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ } ባሉት (አስር ቀን) ተከታታይ የስራ ቀን ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 8. መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋሞልቶ እና የድርጅቱን ህጋዊ  ማህተም አድርጎ የማያቀርብ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 9. የጨረታውን አሸናፊ ማሸነፋቸውን በጽሁፍ የምንገልጽላቸው ሲሆን ለጨረታ አፈጻጸም ማስከበሪያ ላሸነፉበት እቃ ዋጋ 10% በማስያዝና ውል በመዋዋል የተመረጡትን እቃዎች በሙሉ በውሉ መሰረት ካላቀረቡት በግዢ ህጉ መሰረት መ/ቤቱ ተጠያቂ ያደርጋል፡፡ በጨረታው ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስላቸውል፡፡
 10. . ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል እንደማይችሉ ማወቅ አለባቸው፡፡
 11. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የያዘ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህን ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ጤና ጣቢያ ቀርበው መውስድ ይችላሉ፡፡ 
 12. የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኝበት አድራሻ አራዳ ክ/ከተማ በአታ ጤና ጣቢያ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል፡፡ 
 13. ተጫራቾች የሚያቀርቡአቸው እቃዎች ሎት 2-4 ያለው በሙሉ ኦርጅናል ሳምፕል ወይም ናሙና እና ሎት 5 ያለው ካታሎግ መስሪያ ቤቱ ድረስ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 14. የእቃዎችን ሳምፕል እና ካታሎግ ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታ ውድቅ መሆኑን ማወቅ አለባቸው።
 15. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 

• ለተጨማሪ ማብራሪያ ፡- አድራሻ ከስላሴ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ወረድ ብሎ በስተምስራቅ 100 ሜትር ገባ ብሎ ከመስከረም 1ኛ ደረጃ ት/ቤት አጠገብ ነው 

ስልክ ቁጥር 011-8699041/011-8684810 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡ 

በአራዳ ክፍስ ከተማ አስተዳደር የበአታ ጤና ጣቢያ