ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ 

በምዕራብ ጎንደር ዞን የገንደውሃ ከተማ አስ/ገን/ኢ/ት/ ጽ/ቤት በስሩ ለሚያስተዳድረው ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል የኤሌከትሮኒክስ እቃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ነጋዴዎችን ይጋብዛል፡፡ 

 1. በዘመኑ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው 
 2. የቲን NO / የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፡፡ 
 3. ከ100,000 በላይ ቫት ተመዝጋቢ ለመሆኑ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
 4. ተጫራቾች የቀረቡትን እቃዎች /Spasfication/ በሙሉ መሙላት አለባቸው፡፡ 
 5. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ዋስትና CPO፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም ቦባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም፣ በጥሬ ገንዘብ ማለትም፡- 10,000 (አስር ሺ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ 
 6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100 ብር (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በምዕራብ ጎንደር ዞን በገንደውሃ ከተማ አስተዳደር ገን ኢ/ል/ት/ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመምጣት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ ከ1፡30 ሰዓት እስከ 6፡30 ከሰዓት ከ9፡00 ሰዓት እስከ 12፡00 ሰዓት ማንኛውም ድርጅት በሚቀርበው የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም አድራሻ እና ስልክ ቁጥር በማስቀመጥ የፖስታውን ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 
 7. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት 
 8. የጨረታ አሸናፊው የሚለየው በሎት (በጠቅላላ) ድምር ዋጋ ውጤት ነው፡፡ 
 9. የገንዘብ አከፋፈሉ ሂደት በተመለከተ በራሱ ስም በቼክ ወይንም በጥሬ ገንዘብ የሚከናውን ይሆናል፡፡ 
 10. ማንኛውም አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነታቸው ከተገለፀ በኋላ የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ 10% ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሆኖ በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ዓቃቢ ህግ ጽ/ቤት ውል የሚወስድ ይሆናል ውል ከያዘ በኋላ የሚፈለጉትን እቃዎች የትራንስፖርትና የመጓጓዣ እንዲሁም ሌሎች ወጪ በራሳቸው የሚሸፈን ሆኖ እቃው የስፔስፊኬሽን ችግር ቢኖርበት በራላቸው የሚሸፈን ሲሆን ውል ከያዘ በኋላ የሚፈለጉትን ስራዎች በሚፈለገው ጊዜ ሰርቶ ባያቀርብ ያስያዙት የውል ማስከበሪያ ውርስ ሆኖ በህግ የሚጠየቅ ይሆናል፡፡ 
 11. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ማወቅ ከፈለጉ በቢሮ ስልክ ቁጥር፡-0583310566 ገ/ከ/አስ/ገ/ኢኮ/ል/ት/ ጽ/ቤት ግዥና ፋይ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ድረስ በአካል በመምጣት ቢሮ ቁጥር 2 መጠየቅ ይችላሉ፡፡  
 12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው 
 13. መ/ቤቱ የተጠቀሰውን ዕቃ 20 በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብት አለው 

በምዕራብ ጎንደር ዞን የገንደ ውሃ 

ከተማ አስ/ገን/ኢ/ት/ጽ/ቤት