የጨረታ ማስታወቂያ 

ድርጅታችን ነባሩን ህንፃ ለማሳደስ እና የመኪና ማቆሚያ (Car Parking Shade) ለማሰራት የአገልግሎት ግዥ በአስቸኳይ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው /በሙያው የግንባታ ፈቃድ ያላቸው/፣በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ከሊራንስ ያላቸው፤ በሚፈለገው የሥራ ዘርፍ ተዛማጅ የስራ ልምድ ያላቸው፤ ከከተማ ልማትና ሕንፃ ኮንስትራክሽን የሙያ ፍቃድ ያላቸውና ደረጃቸውም ደረጃ GC-5 or BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተጫራቾች በሶፍት ኮፒ (CD) የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ቢጋር (ToR) 1ኛ ፎቅ ድርጅቱ አዲስ ሕንፃ በሚገኘው ከፋይናንስ ዳይሬከቶሬት ከዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 100.00 ከፍለው በሙግዛት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ በአቅርቦትና ሎጀስቲክ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የፋይናንሻይልና የቴክኒካል የመጫረቻ ሠነዶቻቸውን በተለያየ ኤንቨሎኘ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ሚያዚያ 15 ቀን 2012 ዓ.ም ከሰዓት በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች፤ የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በአቅርቦትና ሎጀስቲክ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል:: ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡ 

ስልክ ቁጥር 011 155 32 33/011-15552 30 

የውስጥ መስመር 345 

ፋክስ ቁጥር 251-11-1-55-3939 

አዲስ አበባ 

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት