የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ 

በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ የኮንታ ልዩ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለኮ/ል/ወ/ሴክተር መ/ቤቶች

 • ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ 
 • ሎት 2 ሞተር ሳይክል 
 • ሎት 3 የቤት ክዳን ቆርቆር 2ኛ ለኮንታ ልዩ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ለሠራዊቱ አባላት የተለያዩ የመኝታ ልብስ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ 

በዚሁ መሠረት ለመጫረት የምትፈልጉ፡

 1. የዘመኑን ግብር የከፈለበት የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፤2/ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣3/ በመንግስት ግዥ ላይ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት፣ 4/የግብር ከፋይነት (ቲን ነምበር) የምስክር ወረቀት፣5/ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ምስክር ወርቀት ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ 
 2. ለሎት 1 እና 2 የስራ ዘርፉ የመልካም ሥራ አፈፃፀም 2011 ዓ.ም በማቅረብ መወዳደር ይኖርበታል፡፡ 
 3. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ 10,000 (አስር ሺህ ብር) ከታወቀ ባንክ በCPO/በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣ 
 4. ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር) በእያንዳንዱ በመከፈል ከኮንታ ልዩ ወረዳ ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 9 መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡ 
 5. ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ 15ኛው ቀን ድረስ በኮንታ ልዩ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ ቤት የጨረታ ዶክመንቶች በመግዛት በዋጋ ማቅረቢያ በመመላት ቴክኒካል አንድ ፖስታ ፋይናንሻል ኦርጅናል አንድ ፖስታ በ2 ኤንቨሎፕ በማሸግና የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ የጨረታ ፖስታውን በኮንታ ልዩ ወረዳ ፋ/ኢኮ/ልማት ጽ/ቤት ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 
 6. የጨረታ ሣጥን የሚከፈተው ከላይ በተባለው በ15ኛው ቀን የሚከፈት ሲሆን ይህ ቀን የመንግሥት ሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮንታ ልዩ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ 
 7. በጨረታ ማስታወቂያ ላይ የተገለፀበትን የመወዳደሪያ ነጥቦችን ያሟላ ብቻ ወደ ቴክኒካል ግምገማ ያልፋል፡፡ 
 8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

ለበለጠ መረጃ :- በቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 047 2270007 ወይም 0472270220 047 227 0386 አድራሻችን፡- በደ/ብ/ብ/ህ/ 

ክ/መ/ኮንታ ልዩ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ከጅማ ከተማ በስተደቡብ 102 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በአመያ ከተማ ይገኛል 

በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ 

የኮንታ ልዩ ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት