የጨረታ ማስታወቂያ 

መለያ ቁጥር ፕ/14/ቤ/ል/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት/08/12 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ፕሮጀክት 14 ቤ/ል/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት 

 • ለሰራተኞች የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጥ ኮድ 3 ሚኒባስ ተሽከርካሪ አገልግሎት፣ 
 • የኮምፒዩተር ፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ማሽኖች ጥገና አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቶች፡ 
 1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ 
 2. በእቃ አቅራቢ ዝርዝር፣በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚችሉ ለመሆናቸው ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ አካል የተሰጣቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፤ 
 3. ለጨረታ ማስከበሪያ ለሰራተኞች የሰርቪስ አገልግሎት ብር 5000 እና ለጥገና አገልግሎት ብር 5000 በፕሮጀከት 14 ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከኦሪጅናል የቴክኒክ ጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 4. የጨረታውን ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 50.00 (ሀምሳ ብር) በመክፈል ከፕሮጀክቱ ክፍያና ሂሳብ ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ 
 5. ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን አገልግሎቶች በመለየት በከፊል ወይም በሙሉ መጫረት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። የሰርቪስ አገልግሎት የሚሰጡባቸውን ሚኒባስ መኪኖች ለቴክኒክ ምልከታ በተጠየቁ ጊዜ የማሳየት ግዴታ አለባቸው፡፡ 
 6. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሀሳብ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የቴክኒክ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በተለያየ ሁለት ፖስታ እንዲሁም ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት በአጠቃላይ አራት ፖስታ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 7፡30 ድረስ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን በፕሮጀከቱ ግዥ እቅድ ዝግጅትና አፈፃፀም ደጋፊ የስራ ሂደት ማስገባት አለባቸው፡፡ 
 7. የጨረታው ሳጥን ጨረታው በወጣ በ10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 7፡30 ተዘግቶ በ11ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፕሮጀክቱ ጽ/ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ እለቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ቅዳሜ ጠዋት እስከ 6፡00 ሰዓት ለፕ/ጽ/ቤቱ የስራ ቀን መሆኑን እንገልጻለን፡፡ 
 8. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
 • ስልክ ቁጥር 0118 28 54 40/0944 74 66 20 
 • አድራሻ፡- ሰሚት ኮንዶሚኒየም ሁለተኛ በር ፊት ለፊት 300ሜትር ገባ ብሎ የፕሮጀክት 14 ቤ/ል/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት አዲስ አበባ 

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 

ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ 

የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን 

ፕሮጀክት 14 ቤ/ል/ቅ/ጽ/ቤት