የጨረታ ማስታወቂያ 

የተያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን ና ልዩ ልዩ መለዋወጫዎችን ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር 03/2012 

መ/ቤታችን በህግ በመፈረስ ላይ ያለው የብሄራዊ መሐንዲሶች ሥራ ተቋራጮች ድርጅት የተረከባቸውን የተለያዩ ዓይነት የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችን እና ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ባሉበት ሁኔታ በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።ስለዚህ 

  1.  በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱንና መመሪያውን ማግኘት ይችላል። 
  2. መለዋወጫዎችና የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን የጨረታ ሰነዱን ከገዙበት ቀን ጀምሮ ኮተቤ በሚገኘው ብሄራዊ መሐንዲሶችና ሥራ ተቋራጮች ድርጅት ግቢ በመገኘት መመልከት ይችላሉ። 
  3. ተጫራቹ ለመጫረት ከሚያቀርበው ዋጋ 10% የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ /Bid Bond/ በባንክ በተመሠከረለት ቼክ /CPO/ በመ/ቤቱ ትክክለኛ ስም በማሠራት ከጨረታ ሠነዱ ጋር በማያያዝና በፖስታው ላይ የተጫራቹን ስምና አድራሻ በመግለጽ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሚያዚያ 06 ቀን 2012 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 3 ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። 
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ . ቤቱ መሠብሠቢያ አዳራሽ ሚያዚያ 6 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡ 00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል። 
  5.  በቂ የዋስትና ማስከበሪያ CPO ያላስያዙ ተጫራቾች ኮሚቴው ከጨረታው የመሰረዝ መብት አለው: .
  6. የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያው ለአሽናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊዎች የጨረታ ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል። 
  7. የኮንስትራክሽን ተሽከርካሪዎች/ማሽነሪዎችን/ የሚጫረቱ ተጫራቾች ማንኛውንም ያልተከፈለ የመንግስት ቀረጥ፤ ግብር፤ የስም ማዞሪያና ሌሎች ወጪዎችን ሙሉ በሙሉ የሚሽፈነው የጨረታው አሸናፊ ይሆናል። 
  8. የጨረታው አሽናፊዎች በውጤቱ መሠረት ክፍያውን ከፈፀሙ በኋላ ያሸነፉባቸውን ንብረቶች በ10 ቀናት ውስጥ አንስተው ማጠናቀቅ አለባቸው በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ሣያነሱ ቢቀሩ ለሚፈጠረው ችግር መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም። 
  9. ከላይ በተጠቀሰው 10ቀናት ውስጥ ንብረቱን አጠናቆ ያልወሰደተጫራች  የመጋዘን ኪራይ በቀን ብር 10 እንዲከፍል ይደረጋል።
  10. መ/ቤቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ  ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 

የመ/ቤቱ አድራሻ፡- የካ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ስልክ ቁጥር 0911201958 ከመገናኛ ወደ ወሰን እና ካራ በሚወሰደው አዲስ አስፋልት ከሰንሻይን ሪል ስቴት ከፍ ብሎ ከሚገኘው መስቀልኛመንገድ ላይ አቤም ሆቴል ፊት ለፊት ነው፡፡በህግ በመፍረስ ላይ ያለ ብሄራዊ መሐንዲሶችና ሥራ ተቋራጮች ድርጅት ሂሳብ አጣሪ 

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ባስአደራ ዳይሬክቶሬት ጄነራል ጽ/ቤት አዲስ አበባ