በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በ2011/12 ምርት ዘመን በድርጅቱ መጋዘን ውስጥ ያለውን የተለያዩ የሰብል ተረፈ ምርቶች/ብጣሪዎች/ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር 0052/ሽያጭ/12 ዓ.ም 

በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት በ2011/12 ምርት ዘመን በድርጅቱ መጋዘን ውስጥ ያለውን የተለያዩ የሰብል ተረፈ ምርቶች/ብጣሪዎች/ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ 

በዚሁ መሰረት፡-

  • ተጫራቶች በሥራ ዘርፉና ሌሎች ተያያዥ ሥራዎች ህጋዊ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸውና የዘመኑን የመንግሥት ግብር አጠናቀው ስለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ 
  • ተጫራቶች ለጨረታው ውድድር ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ /150,000/ አንድ መቶ ሃምሣ ሺህ ብር ብቻ/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ማዘዣ (CPO) ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
  • የጨረታው ሰነድይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 150 በመክፈል በሃዋሳ ከተማ በሚገኘው በድርጅቱ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ከፍል ቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይችላሉ። 
  • ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ በሰም በታሸገ ፖስታ /ኤንቨሎፕ በማድረግ ኦሪጂናልና ኮፒውን ለየብቻው ከተጓዳኝ ማስረጃዎች ጋር በማደራጀት በድርጅቱ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በ15ኛው ቀን ከቀኑ እስከ 8፡00 ሰዓት ማስገባት አለባቸው:: 
  • የጨረታው ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በወጣ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት በድርጅቱ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 12 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይከፈታል፡፡ 
  • ድርጅቱ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
  • በስልክ ቁጥር፡- 046 220 1752/2285/2117 

በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት 

የደቡብ ምርጥ ዘር ድርጅት 

ሃዋሳ