ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በ2012 በጀት ዓመት የማሽነሪዎች ግዥ : የስፖርትና ጅምናዚየም ዕቃዎች : የተለያዩ ህትመቶች ግዥ :የሕክምና ቋሚና አላቂ የላብራቶሪ ዕቃዎች የደንብ አልባሳት ግዥ :የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግዥ ጨረታ 

ማስታወቂያ ቁጥር WRU 009/2012 

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በ2012 በጀት ዓመት

 • ምድብ 1-የማሽነሪዎች ግዥ
 • ምድብ 2 የስፖርትና ጅምናዚየም ዕቃዎች
 • ምድብ 3 የተለያዩ ህትመቶች ግዥ
 • ምድብ 4- የሕክምና ቋሚና አላቂ የላብራቶሪ ዕቃዎች ግዥ
 • ምድብ 5 የደንብ እልባሳት ግዥ
 • ምድብ 6 የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለሆነም ተጫራቾች በዘርፉ፡ 

 • በመስኩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ለመንግስት ግዥዎች በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን የዌብ  ሳይት መረጃ ፣የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (TIN) ፣ የቫት ሰርተፊኬት እና ለምድብ 4 ተሳታፊዎች ከኢትዮጵያ የምግብ፣የመድኃኒትና ጤና  ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
 • በተጨማሪም የዘመኑን የግብር ግዴታ የተወጡና የከፈሉበትን ማረጋገጫ(ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችሉ፣ እና በመንግስት ግዥ ላይ እንዳይሳተፉ ያልታገዱ መሆን አለባቸው፡፡ .
 • ተጫራቾች ለምድብ 1 ብር 100,000 /አንድ መቶ ሺ ብር/ ፣ ለምድብ 2 ብር 15000/አስራ አምስት ሺ/ ፣ ለምድብ 3 ብር  20000/ ሃያ ሺህ/፣ ለምድብ 4 ብር 100000/አንድ መቶ / ሺህ/ ለምድብ 5 10000/አስር ሺህ 1 ለምድብ 6 20000/ሃያ ሺ/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረ CPO ፣በጥሬ ገንዘብ  የከፈሉበትን ደረሰኝ ወይም በጨረታ ሰነዱ ላይ እና በግዥ መመሪያው  ከተፈቀዱት በአንዱ ከኦርጂናል የጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ .
 • ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች ዩኒቨርሲቲው ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ በራሳቸውትራንስፖርትስማጓጓዝ ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
 • ከላይ የተገለፁትን ማሟላት የሚችሉተጫራቾች ሰነዱን ከዩኒቨርስቲው ግዥ እና ፋይናንስ የስራ ክፍል በመቅረብ ለሰነዱ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ ብቻ በመክፈል መግዛት የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላት ኦርጂናል እና ኮፒ ለየብቻ ስሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን እስከ 8፡00 ድረስ ብቻ በዩኒቨርስቲው በግዥ ቡድን ቢሮ በሚገኘው ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
 • ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም መታዘብ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት በተገኙበት 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ 8፡30 ይከፈታል፡፡ 
 • ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በተለያዩ ምክንያቶች የሚራዘም ከሆነ በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለፅ ይሆናል ፡፡
 • በጨረታው አከፋፈት ሂደት የተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው  አለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት ሂደት አያስተጓጉሉም፡፡ 
 • የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ተጫራቶች በፅሁፍ እና በዩኒቨርሲቲው የውስጥ ማስታወቂያ የሚለጠፍ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
 • ዩኒቨርስቲዉ የተሻለ አማራጭካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ 

ማሳሰቢያ 

 1.  ተጫራቾች በሚሞሉት እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ገፆች እናፖስታ ላይ የድርጅቱ ማህተም፣ ሙሉ አድራሻ ስ/ቁ፣ ፖሳቁ፣ ፋክስ፣ ኢሜይል፤   ወዘተ እንዲሁም የሞላውን አካል ሥምና ፊርማ ማረጋገጥ አለበት – 
 2. የጨረታው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለበት መሆን አለበት 

ለበለጠ መረጃ : በስልክ ቁጥር 046 871 40 16 ይደውሉ 

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ