በደቡብ ብ/ብ/ህ/ከ/መ/ በመሳደታ ዞን ዳሞት ሶሬ ወረዳ ፋ/ኢኮ/ልማት ጽ/ቤት ሕንፃ ግንባታ በግልጽ ጨረታ ተጫራቶችን በመጋበዝ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 

በደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መ በወላይታ ዞን ዳሞት ሶሬ ወረዳ ፋ/ኢኮ/ ልማት ጽ/ቤት በ2012 በጀት ዓመት የዳሞት ሶሬ ወረዳ ፍርድ ቤት በደብዳቤ ቁጥር ዳሶወፍ/0932/12 በ10/07/2012 ዓ/ም ለሚያስገነባው ሕንፃ ግንባታ በግልጽ ጨረታ እንዲወጣ በጠየቁት መሠረት ተጫራቶችን በመጋበዝ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡ 

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች፡-

 1. በኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የተመዝገቡ፤ ደረጃቸው GC/BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆነ፤ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና በ2012 ዓ/ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤ ተ.እ.ታ (VAT)ተመዝጋቢ የሆኑ ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ከሚመለከተው ክፍል የተሰጠ ታከስ ኪሊራንስ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 2. ተጫራቶች ስድስት ወር ያላለፈው የታከስ ክሊራንስ /TAX CLEARANCE/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 3. ተጫራቶች በፌዴራል ግዥ እና የመንግሥት ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡ 
 4. ተጫራቶች የመልካም የሥራ አፈጻጸም በበጀ ዓመት የተሠራ የሥራ አፈጻጻም ማቅረብ የሚችሉና የሥራ ልምዱ የመጨረሻ ዙር ክፍያ የተፈጸመበት፤ ርክክብ ቬርቫልና የጸደቀ የሥራ ውል ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 5. ተጫራቶች ዝርዝር የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምረው ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዶከመንቱ የማይመለስ ብር 300.00/ ሦስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከዳሞት ሶሬ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ ቤት ቢሮ ቁጥር 8 የንግድ ፈቃዳቸውን ዋናውን/ original/በመያዝ መግዛት ይችላሉ፡፡ 
 6. ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናሉና ቴክኒካል ሰነድ ኦሪጅናሉን በአንድ ላይ በማሸግ እና 2 የኦርጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ በመፈረም ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል። 
 7. ተጫራቾች የብቻ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ CPO/100,000.00/አንድ መቶ ሺህ ብር / ከጨረታው ሠነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 8. የጨረታው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ(30)ተከታታይ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ሰዓት በዳሞት ሶሬ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 ይከፈታል፡፡ 
 9. ተጫራቾች በሚያቀረቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለበትም፡፡ 
 10. ተጫራቾች በጨረታ መክፈቻ የዋጋ ንባብና በሂሣብ ማስተካከያ መሀል ያለው ልዩነት ከ2% መብለጥ የለበትም፡፡ 
 11. ተጫራቶች በዞኑ ውስጥ ሊሠ ምንም ዓይነት ማስጠንቀቂያ ያልተሰጠባቸው መሆን አለባቸው፡፡ 
 12. ተጨማሪ እንደገና ተሻሽሎ የወጣው የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 28/2010 እና በዚሁ መመሪያ ላይ ማሻሻያ የያዘ ሰርኩላር ተግባራዊ ይሆናል፡፡ 
 13. ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 
 • ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0462720412/0462720336 

በደቡብ ብ/ብ/ህ/ከ/መ/ በመሳደታ ዞን 

ዳሞች ሶሬ ወረዳ ፋ/ኢኮ/ልማት ጽ/ቤት