ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ

ቁጥር 01/2012

ዲኬቲ ኢትዮጵያ ቀረጥ የተከፈለባቸው, አምስት ዓመት እና ከዚያ በላይ ያገለገሉ 11 ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በዚህም መሠረት፡-

1.    ከገርጂ ወደ ጉርድ-ሾላ በሚወስደው መንገድ ከጉና መጋዘን ቀጥሎ በሚገኘዉ መጋቢ መንገድ ላይ ወጋገን ባንክ ገባ ብሎ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን የማይመለስ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፡፡

2.    ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጠዋት ከ 3:00-5:30፤ ከሰዓት ከ 7:00 እስከ 10:30 ባለው ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎቹን ከላይ በተገለጸው የድርጅቱ መጋዘን ግቢ ውስጥ ማየት ይቻላል፡፡

3.    ተጫራቾች መግዛት ለሚፈልጓቸው ተሽከርካሪዎች የሚያቀርቡትን ዋጋ በተዘጋጀው ቅጽ ላይ በመሙላት ኤንቨሎፕ ውስጥ ከተው በማሸግ በድርጅቱ መጋዘን ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም. 3:00 (ጠዋት) ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡

4.    ተጫራቾች ለሚጫረቱት እያንዳንዱ ተሽከርካሪ የሚያቀርቡትን ዋጋ ሃያ በመቶ (20%) በዲኬቲ ኢትዮጵያ ስም በተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (ሲ.ፒ.ኦ.) የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው። ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘ ገንዘብ ለአሸናፊ ተጫራቾች መክፈል ከሚኖርባቸው ጠቅላላ ዋጋ ላይ ተቀናሽ የሚደረግ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ይመለሳል፡፡ 

5.    ጨረታው መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም. ከረፋዱ 3:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መጋዘን ግቢ ውስጥ ይከፈታል፡፡   

6.    የጨረታው አሸናፊዎች የጨረታ ውጤቱ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ ያሸነፉበትን ሙሉ ዋጋ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ በመክፈል ተሽከርካሪዎቹን ማንሳት አለባቸው፤ ቀሪ ክፍያ ፈጽመው ያሸነፉትን ተሽከርካሪ ለማይወስዱ አሸናፊዎች ለጨረታ ማስከበሪያ የከፈሉት ገንዘብ አይመለስም፡፡

7.    የጨረታው አሸናፊዎች ቀረጥን ጨምሮ ያሸነፏቸውን ተሽከርካሪዎች ባለቤትነት ወይም ስም ለማዘዋወር የሚያስፈልጉ ማንኛቸውም ክፍያዎችን እና ወጭዎችን ይከፍላሉ፡፡

8.    ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት በሕግ የተጠበቀ ነው።

9.    ተጨማሪ ማብራሪያ፤ በስልክ ቁጥር 011 663 22 22 ወይም 09 11 23 13 31 / 0911 60 90 83 / 0911 65 17 37 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ዋናው ቢሮ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 177 ኢትዮ ቻይና የወዳጅነት መንገድ ተባበር በርታ ህንፃ ፊት ለፊት 2ኛ እና 3ኛ ፎቅ ላይ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ፡ ስልክ ቁጥር፡- 011 663 22 22 / 0911 23 13 31 / 0911 60 90 83