የግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ጳጉሜ 4 /2011 ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል

የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2012 በጀት ዓመት ክፍል

 1. የጽህፈት መሣሪያዎች
 2. የጽዳት ዕቃዎች
 3. የደንብ ልብስ
 4. የመኪና ጌጣጌጥ ከአቅራቢ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት

 1. የዘመኑ ግብር የከፈሉበት የታደሰ ንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር / TIN /ሰርተፍኬት የሚያቀርቡ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
 2. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ለ21/ሃያ አንድ/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ምሥራቅ ሪጅን ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር104 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን ሰነዱ የድርጅቱ ሕጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በድርጅቱ ባለቤት ወይም ወኪል ተፈርሞ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 22ተኛው ቀን 8፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይቻላል፡፡
 3.  የጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
 4.  ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በተለያዩ ፖስታዎች ማሸግ ይኖርባቸዋል፡፡
 5.  ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስረከቢያ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ የተረጋገጠ CPO ፤ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከዋጋ ማቅረቢያ ሠነዶች ጋር አብሮ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
 6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ21/ለሃያ አንድ/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ22ኛው ቀን ጳጉሜን 4 /2011 ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሪጅኑ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 202 ይከፈታል። ነገር ግን የጨረታ መክፈቻ ዕለት በበአላትና ዕረፍት ቀን ዝግ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
 7. የጨረታ ሰነዱ የሚዘጋጀው በአማርኛ ይሆናል፡፡
 8. አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
 9. ጨረታውን የሚያሸንፉ ተጫራቶች ዕቃውን እስከ ሪጅን ጽ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ድረስ ማምጣት ይኖርበታል፡፡
 10. ሪጅኑ ጽ/ቤቱ ለጨረታው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ፡- የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት ድሬዳዋ

ስልክ ቁጥር 0254-11-00-94

ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

የግል ድርጅቶች ሠራተኞች ማህበራዊ

ዋስትና ኤጀንሲ ምስራቅ ሪጅን ጽ/ቤት