• Pending

Guna Begemider Woreda FEDB

Be'kur Hidar 7, 2013

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጉና በጌምድር ወረዳ ገ/ኢ/ት/ፅ/ቤት የግዥ ቡድን ለጉና በጌምድር ወረዳ ገጠር መንገድ ትራንስፖርት ፅ/ቤት በገጠር ቀበሌዎች ለመጓጓዣ እና ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ በመደበኛ ካፒታል ና በመደበኛ በ2013 በጀት ዓመት

 • ሎት 1. ለመንገድ ቆረጣና ጠረጋ ስራ ካት ኤክስካቫተር ፤ካት ደዘር ፤ካት ሎደር ፤ካት ግሪደር ፤ሮሎ ባለ 14 ቶን በአጠቃላ የማሽን ኪራይ ተከራይቶ ለማሰራት፣
 • ሎት 2. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
 • ሎት 3. የፅዳት እቃዎች፣
 • ሎት 4. ሲኖ 16ሜትር ኩብ የሚይዝ ተከራይቶ ለማሰራት ፣
 • ሎት 5. የስፓርት ትጥቅ በግልፅ ጨረታ በሎት አወደድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች

የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የም ትችሉ መሆኑን ይጋብዛል ፡፡

 1.  በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 3. . የግዥ መጠኑ ከብር 200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ /የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 5. የማሽኖቹ ማጓጓዣ፤ነዳጅና ሌሎች የተለያዩ ወጭዎች በባለሃብቱ ወይም በአሸናፊው ግለሰብ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
 6. ማሽኖቹ በስራላይ እያለ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ቢቆምና ቢበላሽ ወጭዎች በባለሃብቱ የሚሸፈኑ መሆኑን እና ማንኛውንም ጥቃቅን ችግር የማንሸፍን መሆኑን፡
 7. . ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ ጉና በጌምድር ወረዳ ገ/ኢ/ት/ዋ/ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 31 ድረስ በመምጣት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 50/አምሳ ብር ብቻ / በመክፈል ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
 8.  ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡ ቢሆንም ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ ሂደቱ ላይ ቢገኙም ባይገኙም ከመክፈት አያግድም፡፡
 9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስት ቢድ ቦንድ /ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ድምር 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዛዝ/ ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በአማረኛ የተተረጎመ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመሂ -1 ገቢ በማድረግ ኮፒውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ የሚችል፡፡
 10. . ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆነ ኦሪጅናል /ዋና/ በታሸገ ፖስታ ጉ/በ/ወ/ገ/ኢ/ት/ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 17 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን የገዙትን የጨረታ ሰነድ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይቻላል፡፡
 11. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ከ5 ተከታታይ ቀናት በኋላ ባሉት በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ከውል ሰጭ መ/ቤቱ ቀርቦ ባሸነፈበት ገንዘብ መጠን የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መውሰድ ያለብዎት ሲሆን በወቅቱ ቀርቦ ውል ካልወሰደ በግዥ መመሪያው 1/2003 መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፡
 12. . የሚገዙትን እቃዎች ወይም ኪራይ ከጠቅላላ ዋጋው ላይ 20 በመቶ የመቀነስና የመጨመር መብት አለው፡፡
 13. በጨረታ ሰነዱ ላይ ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ከሆነ ተቀባይነት የለውም ከውድድር ውጭ ነው የሚሆነው፡፡
 14. የሚገዙትን እቃዎች ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን ከመጫረቻ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
 15. ርክክቡ የሚፈፀመው በጥራት ማረጋገጫ ሙያተኛ ተረጋግጦ ነው፡፡
 16. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የባዕል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
 17. የጨረታ አሸናፊው የሚለየው በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላ ይሆናል፡፡
 18. ከማሽኖቹ ውጭ ያሉት እቃው የሚ ቀርበው ጉና በጌምድር ወረዳ ክምር ድንጋይ ከተማ ድረስ ነው፡፡
 19. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
 20. ለበለጠ ማስረጃ በስልክ ቁጥር 0582510226 ደውለው ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
 21. . ማሳሰቢያ፡- አሸናፊ ድርጅቱ ወይም አቅራቢው ማሸነፉ ተገልፆለት ለሚያቀርባቸው እቃዎች በጥራትም ሆነ በመጠን የተጠየቀውን እቃ ውይም ማሽን ለማቀረብ ፍቃደኛ ያልሆነ እና ለማጭበርበር የሚሞክር ካለ በግዥ መመሪያው 1/2003 መሠረት አስፈላጊውን እርምጃ ይወስዳል፡፡

የጉና በጌምድር ወረዳ ገ/ኢ/ት/ፅ/ቤት