Gurage Zone F/E/D/Bureau

Addis Zemen Tir 30, 2013

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 8/2013

የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለጉራጌ ዞን ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ በወልቂጤ ከተማ የባህል ቡድን መለማመጃ አዳራሽ ቀሪ ስራዎች ግንባታ ስራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በማመልከቻ ሲጠየቁ፡

 1. ደረጃቸው ቢሲ/ጂሲ-7 እና ከዚያ በላይ ፍቃድ ያላቸው ፤
 2. የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ያደሱ ሆነው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፤
 3. የዘመኑን የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡
 4. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆነ ከድርጅቱ፡ ህጋዊ ውክልና ይዘው መቅረብ አለባቸው ፤
 5. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ጉራጌ ዞን ገቢዎች ባለሥልጣን ዋና ቅ/ፅ/ቤት በመክፈል ሰነዱን ጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፤
 6. ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት ሲያቀርቡ፡
 7. ሀ/ ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒዎች እያንዳንዳቸውን በሰም በማሸግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናትፖስታ በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያ 5000 /ሃምሳ ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፣ ቢድ ቦንድ ከሆነ ለ120 ቀናት የሚቆይ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከኦሪጅናል ዶከመንት ጋር በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት
 8. ለ/ ለፋይናንሺያል ዶክመንት አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ በሰም በማሸግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ ውስጥ በማሸግ ፋይናንሺያል በሚል በመለየት እስከ 21ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው ፣
 9.  የጨረታው ማስከበሪያ ሲፒኦ በጉራጌ ዞን ፋኢ/ል መምሪያ ስም መሰራት አለበት፣
 10. ከተራ ቁጥር 1-7 የተጠቀሱትን መስፈርቶች መለ ለሙሉ ያላሟላ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይሆናል፤
 11. ጨረታው ቴክኒካል ዶክመንት በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
 12. የፋይናንሺያል /የፕሮጀክቱ ግንባታ ዋጋ ከቴክኒክ ግምገማ ውጤት በኋላ የቴክኒክ ግምገማውን ያለፉት ተጫራቾች ሰነድ ብቻ የጨረታው ኮሚቴው በማስታወቂያ በሚገልፀው ቀን ይከፈታል፤
 13. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡

ማሳሰቢያ

 1. በአፈፃፀም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መወዳደር አይችሉም፡፡
 2. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፋል፡፡
 3. ዞኑ በሚከታተላቸው ፕሮጀክት ከሁለት በላይ ፕሮጀክት ያላቸው መወዳደር አይችሉም፡፡

ለበለጠ መረጃ 011330-01-12

የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

ወልቂጤ