• Pending

የጨረታ ማስታወቂያ

የጅማ ዩኒቨርሲቲ 2013 . ለዩኒቨርሲቲው ፖሊስ የደንብ ልብስና የቪዲዮ ኮንፈረንስ ሲስተም በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::

ስለዚህ በዚህ መሠረት በጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛወም ሕጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ የእቃና የምክር አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ በዘመኑ የታደሰ አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃድ የሀገር ውስጥ ገቢ የድጋፍ ደብዳቤ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀትና ግብር ስለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋጋ ሞልተው ሲመልሱ ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ያለባቸው የብር መጠንና ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው ቀን :

..

የግዥው ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ መጠን

ጨረታው የሚዘጋበት ሰዓት ጧት

የሚዘጋበት ሰዓት ጧት

የጨረታ መክፈቻ ቀን

ሎት 1

ለዩኒቨርሲቲው ፖሊስ የደንብ ልብስ

50,000.00

400

4:15

13/9/2013 .

ሎት 2

የቪዲዮ ኮንፈረንስ ሲስተም

100,000.00

4:00

 

4:15

 

16/9/2013 .

 

 

3 ተጫራቾች ላሸነፉባቸው እቃዎች አቅርቦቱን የሚፈፅመት በራሳቸው የትራንስፖርት ወጪ ጅማ ዩኒቨርሲቲ እቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ነው።

4 ተጫራቾች ማናቸውንም የመንግስት ታክስና የግብር ግዴታዎችን ከነመጓጓዣው በሚያቀርቡት  የእያንዳንዱ የመወዳደሪያ ነጠላ ዋጋ ውስጥ አካተው ማቅረብ አለባቸው።

5 ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በጅማ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በግንባር አስፈላጊ መረጃዎችን ይዞ በመቅረብ የጨረታ ሰነ የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ የኢትዮ ብር) በመከፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ

 

የበለጠ መረጃ ቢያስፈልገዎት በስልክ ቁጥ 047 111 84 00/047 112 38 95 መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

የጅማ ዩኒቨርሲቲ