Jinka University

Addis Zemen Tahsas 28, 2013

 በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የግልፅ ጨረታ ግዥ የመለያ ቁጥር JKU/006/2013 .

 

የጂንካ ዩንቨርሲቲ 2013 የትምርት ዘመን ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለትራንስፖርት አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችን በመከራየት የትራስፖርቴሽን  አገልግሎት ሰራተኞቹ መስጠት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት፡በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች/ ተጫራቾች

 1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
 2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
 3. የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ሊስት (ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
 4.  የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የምስክር ወረቀት፣
 5. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት /TIN/ እና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ከገቢዎች ባለስልጣን ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
 6.  የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ካደራጀው አካል የሚሰጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 7. የመኪና ባለቤትነት ሊብሬ እና የመድን ዋስትና የግል ወይም ህጋዊ ውክልና ሰነድ ከጨረታ ሰነድ ጋር አብሮ ማቅረብ የሚችል፡፡
 8.  የሾፌርና የረዳት ደመወዝ የመኪና ጥገና ቅባትና ዘይት ባለቤቱ ለመሸፈን ፍቃደኛ የሆነ
 9. ስለጨረታው የሚገልጸውን የጨረታ ሰነድ ከጅንካ ዩኒቨርሲቲ ግዥ ዳይሬክቶሬት ህንፃ 2 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 107 እና አዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ ከአሜሪካን ኤምባሲ ፊት ለፊት ከቀድሞ የኢትዮጵያ መጽሐፍት ማከፋፈያ ድርጅት ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሚገኘው ጊዜያዊ ቢሮ ቁጥር 30 ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ ለእያንዳንዱ ምድብ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ለመግዛት መወዳደር የምትችሉ ሲሆን ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተቋቋመበትን የህጋዊነት ማስረጃ በማሳየት ያለክፍያ በነፃ ይሰጣቸዋል፡፡
 10. ከአዲስ አበባ ጊዜያዊ ቢሮ የጨረታ ሰነድ የሚወስዱ ተጫራቾች የሰነድ መግዣ ገንዘቡን ለጂንካ ዩኒቨርሲቲ በስሙ በተከፈተ የኢት.ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000241842499 ገቢ ያደረጉበትን ክሬዲት አድቫይስ /Credit Advice/ ብቻ በማቅረብ መውሰድ ይቻላል፡፡
 11. የጨረታው ሰነድ ማስታወቂያው ታትሞ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ለአስራ አምስት/15/ ተከታታይ የስራ ቀናት የሚሸጥ ሆኖ በአስራ ስድስተኛው 16ኛው ቀን /የስራ ቀን ሲሆን ብቻ ከሰዓት በኋላ 900 ሰዓት በጂንካ ዩኒቨርሲቲ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 307 በተዘጋጀ ሳጥን ገብቶ ይታሸግና 930 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ የተጫራቾች ወይም የህጋዊ ወኪሎቻቸው በወቅቱ ያለመገኘት ጨታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
 12. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የቴክኒክ ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በሰም በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ አሽገው እና የፋይናንሻሉንም ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በሰም በማሸግ ባንድ እና ፖስታ አሽገው የእቃውን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በመሙላት የተጫራቹን ድርጅት ማህተም በማድረግ በአግባቡ ተፈርሞ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ከላይ በተራቁ 15 ላይ የተገለፀው ቀን ቦታና ሠዓት ማቅረብ  ይጠበቅባቸዋል፡፡
 13. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ያለባቸው 90 /ዘጠና/ ቀናት የሚሆን /ሲፒኦ/ CPO ወይም በግዥና መመሪያ አንቀፅ 16.16.4 ላይ በተገለጸው መሰረት ተገቢውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከመጫረቻ ዋጋው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ካደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል :: የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና

 • ሎት1ባለ 63 ወንበር መኪና -13,000 አስራ ሶስት ሽህ ብር/
 • ሎት -2-ባለ 45 ወንበር መኪናዎች-12,000/አስራ ሁለት ሺህ ብር/
 • ሎት3- ባለ 29 ወንበር መኪናዎች 11,000/አስራ አንድ ሺህ ብር/
 • ሎት4- ሀይላክስ ደብል ጋቢና መኪናዎች 10,000 /አስር ሺህ ብር/
 • ሎት 5- ባለ1 ጋቢና መኪናዎች 9,000 /ዘጠኝ ሺህ ብር
 • ሎት 6- ላንድ ኩሩዘር ቫን መኪናዎች 9,000 /ዘጠኝ ሺህ ብር
 • ሎት 7- ሚኒባስ 12 እና ከዚያ በላይ መጫን አቅም ያለው መኪና 9000 /ዘጠኝ ሺህ ብር

15 የጨረታው አሸናፊ ድርጅት የተሽከርካሪውን የቴክኒክ ምርመራ ውጤት በማቅረብ ከዩኒቨርሲቲው ጋር ውል በመግባት ማንኛውንም ወጪ በራሱ ችሎ የሚያቀርበውን እቃ ተሽከርካሪ ያስረከባል።

16. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ ከዚህ በታች በተጠቀሱ አድራሻዎች ደውሎ መጠየቅ ይቻላል

ስልክ ቁጥር፡– 0916475050 እና 0926481917

የጂንካ ዩኒቨርሲቲ