Dire Dawa Administration Public Procurement and Property Disposal Service

Addis Zemen Tir 24, 2013

የጨረታ መክፈቻ ጊዜ ማራዘሚያ ማስታወቂያ

በድሬደዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት /ቤት ለአስተዳደሩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች፤ ቢሮዎች /ቤቶች እና ቀበሌዎች አገልግሎት የሚውሉትን የተለያዩ ኤሌክትሮኒክሶች ፈርኒቸሮች የደንብ አልባሳቶች የደንብ ጫማ እና የስራ መሳሪያዎችን በማእቀፍ ግዥ ለመፈጸም በጨረታ መለያ ቁጥር 004/2013 በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጥር 5 ቀን 2013 . ማውጣቱ ይታወሳል

በዚሁም መሠረት የጨረታ ሠነዶቹን በመሸጥ ላይ እያለን የፈርኒቸር ጨረታ ሠነድ ላይ መስሪያ ቤቱ ማሻሻያ ማድረግ ስለፈለገ የጨረታ ሰነዱን ለገዙት ተጫራቾች በቂ ጊዜ መስጠት እንዳለበት ስለታመነበት ይህ ከላይ በተጠቀሠው ቀን እና የጨረታ መለያ ቁጥር ከወጡት ዝርዝር የማእቀፍ ግዥዎች መካከል የፈርኒቸርን ብቻ የጨረታ መክፈቻ ቀን እንዲራዘምልን ስለፈለግን ጨረታው ሐሙስ የካቲት 18 ቀን 2013 ዓም ከጠዋቱ 400 ታሽጎ በዚሁ እለት 430 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የምንከፍት መሆኑን እንገልጻለን።

የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት /ቤት