• Wollo

Dawut Woreda FEDB

Addis Zemen Tahsas 4, 2013

 

የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ መስተዳደር ዞን መምሪያ የዳውንት ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ትብብር /ቤት የግዥናንት/አስ/ ቡድን፡፡ ለሴክተር /ቤቶች በመደበኛ በጀት የተለያዩ እቃዎች፡ ማለትም፡

 • 1/የፅህፈት መሳሪያ፣
 • 2/የመኪና እቃ መለዋወጫ፣
 • 3/የደንብ ልብስ (የተዘጋጁ ልብሶችና ጣቃ ጨርቅ)
 • 4/የንጽህና መስጫ እቃዎች፣
 • 5 የተለያዩ ጫማዎችና ቦርሳዎች፣
 • 6/የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች፣
 • 7 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እቃ ግዥ ለመፈፀም ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውን

በግልፅ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አወዳድሮ የእቃ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል ስለዚህ የዳውንት ወረዳ ////ቤት የግዥና ንብረት አስ/ ቡድን የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቶችን ለማወዳደር ይጋብዛል፡

 1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /tin no/ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ ለየብቻው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 2.  የግዥው መጠን ከብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆኑ የተጨማሪ እሴት ታስክ /ቫት/የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል የሚሞሉትም ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ከፍያ ትዛዝ /Cpo/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ ህጋዊ ደረሰኝ ተቆርጦ ከሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው
 4. በማንኛውም ግዥ ለእቃዎች ከብር 10,000/አስር ሽህ ብር በላይ/እና ለአገልግሎት ግዥ ብር 3000/ ሶስት ሽህ ብር በላይ/2 % የቅድመ ግብር ተቀንሶ ገቢ ይደረጋል፡
 5. ተጫራቾች ከላይ ለተገለፁት የእቃ አቅርቦቶች የጨረታ ሰነድ ቢሮ ቁጥር 15 እራሳቸው ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ፈቃዳቸውን በማሳየት ብር 50 (አምሳ ብር ብቻ) በመክፈል ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
 6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን እና የንግድ ፈቃድ መረጃቸውን ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻው በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ የጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ  ሲሆን እስከ16ኛው ቀን 330 ሰዓት ድረስ ዘወትር በስራ ሰአት /////ትብብር /ቤት ቢሮ ቁጥር 15 በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
 7. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከጧቱ 400/ሰዓት፤ይከፈታል፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ለመከፈት አያስተጓጉለውም የበአል ቀን ከሆነ ለቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
 8. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው የስራ ዝርዝር በመግለጫው መሰረት በሰነዱ በእያንዳንዱ በግልፅ ዋጋውን መሙላት እና የድርጅታቸውን አድራሻ፤ስም፣ማህተምና ፊርማ ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
 9.  ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ካሉ በክልሉ የግዥ አዋጅ 179/2003 እና በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ከጨረታ ውጭ እንደሚደረጉ፣ ያስያዙቱን የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ እንደሚደረግ እና በተመሳሳይ ሌላ ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል፡
 10. ተጫራቾች የጨረታ ውድድሩ ጠቅላላ ድምር ዋጋ መሆኑን ማወቅ ይኖርባቸዋል፡
 11. በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተደራጁ ከቴከኒክና ሙያ ተቋማት ስለአደረጃጀታቸው የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው ፡፡
 12. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን እቃ ዳውንት ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር /ቤት ኩርባ ከተማ ድረስ በማቅረብ እርክክቡ በባለሞያ እየተረጋገጠ የሚፈጸም ይሆናል፡
 13. የጨረታ ሰነዱን በጥራት ያልተሞላ ስርዝ ድልዝ ያለው የማይነበብ ለሶስተኛ ወገን ግልፅ ያልሆነ ሰነድ ከውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
 14.  ከጨረታ መዝጊያ የመጨረሻ ስአት በኃላ ዘግይቶ የደረሰ የመጫረቻ ሰነድ አሽጎ ሳይከፈት ወዲያውኑ ለተጫራቾቹ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
 15. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የእቃ አቅርቦት የምስከክር ወረቀት ከሰነዳቸው ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡
 16. በጨረታው ያሸነፉ ተጫራቶች ውል ሲወስዱ ቅድሚያ ክፍያ ለሚወስዱት ገንዘብ 30% እኩል ዋጋ ያለው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ( CPO) የሚያሲዙ ሲሆን፡ ለውል ማስከበሪያ 10% ለሚያሲዙት ገንዘብ ቅድሚያ ክፍያ ከታዎቀ ባንክ የሚሰጥ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ ህጋዊ ደረሰኝ ተቆርጦ ከሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው ::
 17.  አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ጀምሮ 5 የስራ ቀናት  በኋላ 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10/00/አስር በመቶ/ለዳውንት ወረዳ ///ትብብር /ቤት በማስያዝ ውል መውሰድ/መፈረም/ይኖርባቸዋል፡ ነገር ግን በተገለጸላቸው ቀን ውሉን ያልፈረሙ የጨረታ አሸናፊዎች የጨረታ ማስከበሪያው ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
 18. ተጫራቾች በጨረታው ውጤት ቅር ከተሰኙ የጨረታ ውጤቱ በማስታወቂያ ቦርድ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅሬታቸውን በየደረጃው ላለ የፋይናንስ ተቋማት ማቅረብ ይችላሉ፡፡
 19. ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ ቢፈልጉ ቢሮ ቁጥር 15 ድረስ በመምጣት/ በስልክ ቁጥር 033 891 60 67 /በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
 20. ተጫራቾች የአሸነፉበት ዋጋ እንደተጠበቀ ሆኖ /ቤቱ መጠኑ 20% የመጨመር ውይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
 21. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡

የዳውንት //// ትብብር /ቤት

የግዥ /አስ//ቡድን

ኩርባ