• Gondar

Durbete Elementary Hospital

Be'kur Tahsas 19, 2013

 

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በም/ዕ/ጎ/ዞ/አስ/ ዞን በደቡ/አቸ/ወረዳ የዱርቤቴ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2013 በጀት አመት አጠቃላይ ዓመታዊ ግዥ ለመፈጸም ማለትም፡

 • ሎት1 የፅህፈት መሳሪያ፣
 • ሎት2 የፅዳት እቃ፣
 • ሎት3 የኤሌክትሮኒክስ እቃ፣
 • ሎት4 የደንብ ልብስ ፣
 • ሎት5 የደንብ ጫማ፣
 • ሎት 6 ህትመት
 • ሎት 7 የዉሀ እቃ
 • ሎት8 የመኪና ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

ስለሆነም መወዳደር የምትችሉ ማንኛውም ተወዳዳሪ (ተጫራች) ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያማሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ::

 1. በዘመኑ የታደሰ እና በዘርፋ የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት/
 2. የግብር ከፍይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያለው /ያላት/
 3. የግዥው መጠን ከብር 200 ሽህ ብር እና ከዛ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
 4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና ሌሎች ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሠነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት ::
 5. የጨረታ ሰነዱን ደ/አቸ/ወረዳ ዱርቤቴ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 03 ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ ::
 6. የጨረታ ዝርዝር መረጃ (እስፔስፈኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላሉ ::
 7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ቢፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
 8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ውጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በየምድቡ (በእየሎቱ ) በተለያዩ ፖስታ በማድረግ በጥንቃቄ በማሽግ ደ/አቸ/ወረዳ ዱርቤቴ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢ/ቁጥር 03 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ማስገባት ይቻላሉ::
 9. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በበኩር ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ከጧቱ 4፡30 ህጋዊ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልፅ ይከፈታል:: በተጨማሪ በጨረታ ሂደቱ በተላለፉት ዉሣኔዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 ተገዥ ይሆናል :: የመክፈቻዉ ቀን በአል ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል::
 10. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የቅሬታ ቀናት በኃላ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸበፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርበታል :: በተባለዉ ቀን ዉስጥ ውል የማይዝ ከሆነ ግን ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ውርስ ይሆናል ::
 11.  ጨረታዉ የሚካሄደው በየሎቱ ጥቅል ድምር ስለሆነ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሎት ሁሉንም መሙላት ይጠበቅባቸዋል:: እንዲሁም የተጠየቀዉን እስፔስፊኬሽን በራሡ መቀየር አይቻልም ስርዝ ድልዝ የበዛበት መሆን የለበትም :: በስህተት ከተሠረዘ በማያጠራጥር ሁኔታ ፓራፍ ማድረግ አለበት ::
 12.  አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች የማውረጃ እና የማስጫኛ እንዲሁም የትራንስፖርት ወጪውን ችሎ ደ/አቸ/ወረዳ ዱርቤቴ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድረስ ማቅረብና ንብረት ክፍል ማስረከብ ይኖርበታል::
 13. የሠነድ መሸጫ ዋጋ ለእያንዳንዱ ሎት 50 ብር በመክፈል መግዛት የሚችሉ ሲሆን በኢንተር ፕራይዝ የተደራጁ ከሆነ ግን በነፃ መዉሠድ ይችላሉ ::
 14. መ/ ቤቱ ባወጣዉ ጨረታ ላይ 20 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠቀ ነዉ ::
 15. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
 16. ሁሉም ተጫራቾች የግዥ ደንብና መመሪያን ማክበር ይኖርባቸዋል::

ለበለጠ መረጃ ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት በአካል ቢሮ ቁጥር 03 ወይም በስልክ 0582230752 መጠየቅ ይችላሉ::

ዱርቤቴ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል