Deneba TVET College

Addis Zemen Tahsas 7, 2013

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ የደነባ ቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ኮሌጅ 2013 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ የሥልጠናና የቢሮ እቃዎች፤

 • ሎት 1የፅህፈት መሳሪያዎችና የፅዳት እቃዎች፣
 • ሎት 2የኮንስትራከሽን /የህንፃ መሳሪያዎች/
 • ሎት 3የኤሌክትሪክና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
 • ሎት 4ኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች፣
 • ሎት 5ብትን ጨርቅ እና ተዛማጅ እቃዎች፣
 • ሎት 6 የተዘጋጁ ልብሶች፣
 • ሎት 7የግብርና እቃዎች፣
 • ሎት 8 የአውቶሞቲቭ የሥልጠና እቃዎች፣
 • ሎት 09አነስተኛ ማሽነሪዎች አና መለዋወጫ እቃዎች፣
 • ሎት 10የደንብ ልብስ ጫማ፣
 • ሎት 11የህክምና እቃዎች፣
 • ሎት 12የምንጣፍና መጋረጃ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መሥፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡

 1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
 2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
 3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ ያላቸው
 4. የግዥው መጠን ብር 200000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ. 1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 6. የሚገዙ እቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /እስፔሲፊኬሽን/ በጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር ሎት 1 2 እና ሎት 3 ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ሎት 4 ሎት 5 ሎት 6 ሎት 7 ሎት 8 ሎት 9 ሎት10 ሎት 11 ሎት 12 ብር 50 /ሃምሣ ብር/ በመክፈል ከኮሌጁ //ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 ማግኘት ይችላሉ።
 8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1 % ከተጨማሪ እሴት ታክ ጋር በባንክ በተረጋገጠ ትከክለኛ  የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በህጋዊ ደረሰኝ መሂ-1/ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
 9. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጨረታ ሰነዳቸው ላይ የተወዳዳሪውን ሥም አድራሻ የሚመለከተው ህጋዊ ወኪል የፈረመበት የተሟላና ማህተም ያረፈበት መሆኑን እና ሥርዝ ድልዝ የሌለበት መሆኑን አረጋግጠው ኮፒና ኦርጅናል በማለት  ማቅረብ አለባቸው፡፡
 10. ተጫራቾች በዘርፉ አንዲወዳደሩ የሚያስችል ንግድ ፍቃድ እስካላቸው ድረስ በአንድ ወይም ከአንድ በላይ ሎት መወዳደር  ይችላሉ፡፡
 11. ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው 5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10 % ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር በባንክ በተመሠከረ ትከከለኛ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በህጋዊ ደረሠኝ (መሂ-1) በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው፡፡
 12. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች ሙሉ በሙሉ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
 13. ተጫራቾች በአንድ ሎት ላይ ያሉ እቃዎች ነጣጥሎ መጫረት አይችሉም፡፡
 14. አሸናፊው ተጫራች ያሽነፈባቸው እቃዎች በራሱ ወጪ በማጓጓዝ ኮሌጁ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
 15.  ኮሌጁ በግዥው ላይ 20% የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
 16.  ኮሌጁ ለመንግሥት በሚያመች አኳኋን ውድድሩን በነጠላ ወይም በጥቅል የማወዳደር መብት አለው፡፡
 17. ተጫራቾች በሌሎች ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ከጨረታ ያሰርዛል፡፡
 18. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለተጫራቾች ከፍት ሆኖ 16 ቀን ከጠዋቱ 400 ታሽጎ በእለቱ ከጠዋቱ 420 ሰዓት ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም የሚከፈት ሲሆን እለቱ በዓል ከሆነ  በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
 19. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብት አለው::
 20. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለገ ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር፡– 09-12-09-10 / 09-10-05-18-32/ 09-23-77-23-23/09-10-22-11-24 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
 21.  የኮሌጁ አድራሻ ከአዲስ አበባ በደብረ ብርሀን ዞሮ ደነባ ከተማ ለመድረስ 170 ኪሎ ሜትር ከአዲስ አበባ በሙከጡሪ መሥመር ዞሮ ደነባ ከተማ ለመድረስ 130 ኪሎ ሜትር፤ ከአዲስ አበባ በሸኖ ተገንጥሎ በአ ቢቂላ መንገድ ደነባ ከተማ ለመድረስ 129 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን

ሸዋ ዞን በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ የደነባ

ቴክኒክና ሙያ ማሠልጠኛ ኮሌጅ