Debire Birihan University

Addis Zemen Tahsas 17, 2013

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DBU29/2013

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ 2013 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ቀጥለው የተዘረዘሩትን አቅርቦቶችን ማለትም

 • ምድብ 1 የህትመት አገልግሎት ለአንድ ዓመት የማዕቀፍ ግዥ
 • ምድብ 2 የመኪና ጎማ፣ ዘይትና ቅባቶች ግዥ /በድጋሚ የወጣ
 • ምድብ 3 የአፈር ምርመራ አገልግሎት ግዥ ከዘርፉ ከተሠማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

በመሆኑም በጨረታው ለመሣተፍ፡-

ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ ሆነው የዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር  ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ በዘመኑ ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሠጠ ክሊራንስ እና የአቅራቢነት ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::

 1. ተጫራቾች በሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለምድብ 1 ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ለምድብ 2 ብር 50,000 /ሃምሣ ሺህ ብር፣ ለምድብ 3 ብር 20,000/ሃያ ሺህ/ በባንክ በተመሠከ ሲፒኦ ወይም በዩኒቨርስቲው በጥሬ ገንዘብ የተከፈለበት ደረሠኝ ወይም የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ከአደራጁ መሥሪያ ቤት የገንዘብ መጠኑ ተጠቅሶ በበላይ ኃላፊ የተፈረመ ደብዳቤ እንደምርጫቸው በአንዱ ከዋናው የዋጋ ሠነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
 2. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ አሥራ አንድ ሰዓት ድረስ ለእያንዳንዱ ምድብ የማይመለስ 100 ብር (አንድ መቶ ብር) በደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ በውስጥ ገቢ ሂሳብ ቁጥር 1000025277515 ላይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በየትኛውም ቅርንጫፍ ገቢ በማድረግና በዩኒቨርስቲው ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 1 ወይም 2 ለትክክለኝነቱ ማህተም በማስደረግ ሠነዱን ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር G-10 ጨረታ ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ።
 3. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን የያዘ የዋ ሠነድ ከምድብ 1 – 2 (Financial documents) ዋናና ቅጂ (original and copy) ከምድብ 3 የዋጋ ሠነድ (Financial documents) ዋናና ቅጂ እንዲሁም ቴክኒካል ሠነድ ዋናና ቅጅ (original and copy) ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎኘ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ብቻ በዩኒቨርሲቲው ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር G-10 በዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
 4. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጎ ምድብ 1 የዋጋ ሠነድ ምድብ 3 ቴክኒካል ሠነድ በዚያው ዕለት 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው፤ ከውስጥ ኦዲት አገልግሎትና ከሥነምግባርና ፀረሙስና ዳይሬክቶሬት ታዛቢ ባለሙያዎች በተገኙበት የጨረታ ሣጥኑ ተከፍቶ በግልፅ ይነበባል ምድብ 2 ለውድድር የቀረቡ ናሙናዎች ባለሙያ ተገምግሞ ከተጠናቀቀ በኋላ ጨረታው ከወጣ በ18ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ላይ ናሙና የተመረጠላቸው እቃዎች  ብቻ የዋጋ ሠነድ ይነበባል የመክፈቻ ቀኑ በሣምንቱ የዕረፍት ቀናት እና በዓላት ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት በግልፅ ይከፈታል ትከከለኛው የመከፈቻ ቀን በጨረታ ሠነዱ ላይ የሚገለፅ ይሆናል
 5. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመሥርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
 6. አሽናፊው ተጫራች ያሸነፋባቸውን ንብረቶች በጨረታ ሠነዱ በተገለፀው መሠረት በራሱ ትራንስፖርት ዩኒቨርስቲው መጋዘን ድረስ በማጓጓዝ ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል
 7. የጨረታው ውጤት ለአሽናፊና ተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሁፍ፤ በስልክ እና በዩኒቨርሲቲው የውስጥ ማስታወቂያ እናሳውቃለን። ተጫራች የጨረታውን ውጤት በስልክ እየደወሉ መከታተልአለባቸው።
 8. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥሮች 011-63-76-147 /011-89 00 -333 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ የግዥና ንብረት

አስተዳደር ዳይሬክቶሬት