Debire Birihan University

Addis Zemen Tahsas 11, 2013

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DBU26/2013

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ2010 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን አቅርቦቶች ማለትም፡-

 • ምድብ 1- የቨርቲካል ሻተር መጋረጃ ጨርቅ እና ተያያዥ እቃዎች  በድጋሚ የወጣ ግዥ
 • ምድብ 2፡- የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች /በድጋሚ የወጣ{ ግዥ
 • ምድብ 3፡- የተለያዩ የኪችን እቃዎች (Kitchen Equipment Dish washing Machine, Hot Water Boiler Machines (Including Installation, Commission in Training) እቃዎች በድጋሚ የወጣ/ግዥ
 • ምደብ 4፡- የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና ጫማ /በድጋሚ የወጣ/ ግዥ እና
 • ምድብ 5፡- የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸር በድጋሚ የወጣ ግዥ ናቸው፡፡ 

ተጫራቾችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም 

በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ፡-

 1. ተጫራቾች በየዘርፉ የተሰማሩ ሆነው በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የማያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
 2. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ለምድብ ፡- 70,000 /ሰባ ሺህ ብር/፤ ለምድብ 2፡30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ለምድብ 3፡ 60,000 /ስልሳ ሺህ ብር/ ለምድብ 4፡- 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ለምድብ 5፡ 70,000.00 /ሰባ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ከሬዲት እንድ ምርጫቸው በአንዱ ወይም በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ፅ/ቤት የተደራጁ ማህበራት ከሆኑ ካደራጃችሁ መ/ቤት የጨረታ ማስከበሪያ የብር መጠን ተገልፆ በመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊ የተፈረመ ደብዳቤ ከዋናው ዋጋ ሰነድ ለምድብ 1, 2 እና 4 እንዲሁም ለምድብ 3 እና 5 ከዋናው የቴከኒካል ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ አስር ሰዓት ድርስ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በደብረ ብርሃን ዩንቨርሲቲ በውስጥ ገቢ በሂሳብ ቁጥር 1000025277515 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በየትኛውም ቅርንጫፍ ገቢ በማድረግ እና በዩኒቨርሲቲው ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 1 ወይም 2 ስለ ትከከለኛነቱ ማህተም በማድረግ ሰነዱን ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር G-10 ጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
 4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ምድብ የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የያዘ ምድብ 3 እና 5 የዋጋና ቴከኒካል ሰነድ ዋናና ቅጅ (Financial & Copy) እና (Technical Documents and copy) እና ምድብ ፣2 እና 4 የዋጋ ሰነድ ዋናና ቅጅ (Financial & Copy) ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ከምድብ 1 እስከ 5 ላሉት በሙሉ በዩኒቨርሲቲው ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር G-10 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ናሙና እንዲቀርብ የተጠየቀባቸውን እቃዎች ጨረታው ከመዘጋቱ ከ4፡00 ሰዓት በፊት በዩኒቨርሲቲው ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር ጂ-10 በማስረከብ የርከከብ መተማመኛ መያዝ አለባቸው፡፡
 5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ጨረታውን መታዘብ የሚፈልግ ማንኛውም አካል በተገኙበት ማስታውቂያው በጋዜጣ በወጣ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ምድብ 3 እና 5 የቴክኒክ ሰነድ የሚከፈት ሲሆን የዋጋ ሰነድ ተጫራቶችና ታዛቢዎች ባሉበት በሌላ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ ይቆያል፡፡ የዋጋ ሰነድ የቴክኒካል ሰነድ ተገምግሞ እንደተጠናቀቀ ውጤቱን ካላወቅን በኋላ የዋጋ ሰነዱ የሚከፈትበትን ቀን በደብዳቤና በስልከ ጭምር ለሁሉም ተጫራቾች የምናሳውቅ ይሆናል፡፡ የምድብ 1, 2 እና 4 ላይ ያሉት ጨረታዎች ናሙና እንዲያቀርቡ የተጠየቀባቸው በመሆናቸው የቀረቡት ናሙናዎች በባለሙያ ተገምግመው እንደተጠናቀቀ በ18ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾችና ታዛቢዎች ባሉበት ናሙና የተመረጠላቸውና ናሙና የማይጠየቅባቸውን የዋጋ ሰነድ በግልፅ ይከፈታል። ቀኑ በሳምንቱ የእረፈት ቀናት ላይ የሚከፈት ሲሆን የመከፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት ውስጥ በጨረታ ሰነድ በሚገለጠው መሠረት ይከፈታል፡
 6. ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
 7. አሸናፊው ተጫራች ንብረቶችን በራሱ ትራንስፖርት በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው አግባብ ዩኒቨርሲቲው ግቢ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
 8. ናሙና ለተጠየቀባቸው እቃዎች ድርጅቱን የሚገልጽ ወይም ማህተም ማድረግ አይፈቀድም ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡ በእያንዳንዱ ናሙና በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን ተራ ቁጥር በመጻፍ ማቅረብና ይጠበቃል፡፡
 9. የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሑፍ በዩኒቨርሲቲው የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳና በደብዳቤ እንገልጻለን፡፡
 10. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻችን ላይ ባስቀመጥናቸው የስልክ ቁጥሮች ዘወትር በሥራ ሰዓት የሚሰሩ መሆኑን አውቀው የጨረታው ሂደት ያለበትን ደረጃ መከታተል ግዴታ አለባቸው፡፡
 11. ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 • ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011 637 61 47 ወይም 011 890 03 33 ግዥ ቡድን ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት

አስተዳደር ዳይሬክቶሬት