Debere Tabore General Hospital

Be'kur Hidar 7, 2013

ግልፅ ጨረታ ማስታዎቂያ

በአማራ ብሔራዊ ከልላዊ መንግስት ጤና ጥበቃ ቢሮ የደብረታቦር ጠቅላላ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚዉሉ

 • የመብራት መለዋወጫ እቃዎች፣
 • የውሃ ቧንቧ መለዋወጫ እቃዎች፣
 • የተለያዩ ፈርኒቸሮች፣
 • የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ጥገና እና
 • የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዝቅተኛ ዋጋ ከሞሉ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል:: ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል::
 1.  በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉና ማቅረብ የሚችሉ::
 2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸዉ የከፋይ ማረጋገጫ የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
 3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያለቸዉና ማቅረብ የሚችሉ::
 4. ተጫራቾች የሚገዙትን እቃዎች ስፔስፍኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ መ/ቤቱ በሚሰጣቸው መሰረት::
 5. ተጫራቾች የሚሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
 6. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 የተጠቀሱትንና የሚፈለግባቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒዉን በጀርባዉ ላይ ከዋናዉ ጋር ተገናዝቧል ብሎ በመፃፍና ማህተም, ስም ፊርማና ቀን በማስቀመጥ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ::
 7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 20 ብቻ ከግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ዉስጥ መክፈል ይኖርባቸዋል::
 8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የእቃዉን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመሂ-1 በመክፈል ማስያዝና ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል::እንዲሁም በሲ.ፒ.ኦ ከሆነ ዋናዉ ሲ.ፒ.ኦ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል::
 9.  ማንኛውም ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ በመሙላት አንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ፖስታዎች ኦርጂናል እና ኮፒ በማለት በአንድ ፖስታ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ላይ ስማቸውንና አድራሻቸውን በመፃፍ በደ/ታቦር ሆስፒታል ውስጥ ከግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሠዓት ማስታዎቂያው በበኩር ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚውል ሲሆን ፖስታውን እስከተገለፀው ቀን ድረስ ማስገባት ይችላሉ::በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ 4፡30 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ውስጥ ጨረታው ይከፈታል:: ነገር ግን 16ኛው ቀን የበዓል እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል::
 10.  በተጨማሪ ሲፒኦ /ጥሬ ገንዘብ ዕንዳያስይዙ ህግ የሚፈቅድላቸዉ ማህበራት ድርጅቶች ከጥቃቅን አነስተኛ ተቋምለኢንስቲዩት በአድራሻ የተፃፈ ማስረጃ ኮፒ ሰነድ ከነ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ ይኖርባቸዋል :: ጥቃቅን ለሆኑ ከተቋቋመ 5 አመት የሞላቸዉ ከሆነ የጨረታ ማስከበሪያም ሆነ የዉል ማስከበሪ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
 11. . የጨረታዉ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ማሻሻያ ማድረግ ወይም በሌሎች ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላትና የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኃላ ከዉድድሩ ራሳቸዉን ማግለል አይችሉም::
 12. ማንኛዉም ተጫራቾች መመሪያን ያልተከተለ አሰራር ሰርቶ የጨረታ ሂደቱን ካወከ ወይም ማሟላት ያለበትን በአግባቡ ካላሟላ ከጨረታዉ ይታገዳል::አሸናፊዎች የሚለዩት በሚያቀርቡት ዝቅተኛ ዋጋ ብቻ ይሆናል::
 13. አሸናፊዎች አሸናፊነታቸዉ እንደተገለፀላቸዉ ቅሬታ ከማቅረቢያ ጊዜ በተጨማሪ ባለዉ አምስት /5/ ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ሆስፒታሉ ድረስ በመምጣት ዉል መዉሰድ ይኖርባቸዋል::
 14. ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም::
 15. አሸናፊዎች የዉል ማስከበሪያ 10 በመቶ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል::
 16. ጨረታው ከመከፈቱ በፊት መቅረብ ያለበት ማስተካከያ ካለ ከ10 ቀናት በፊት ማቅረብ ይቻላል::
 17. ተጫራቾች ሆስፒታሉ አስፈላጊ ሁኖ ካገኘዉ አሸናፊዉን በጥቅል ድምር ሆነ በተናጥል የመለየት መብት mይኖረዋል::ነገር ግን በጥቅል ለመለየት የማይገደድ ይሆናል::መ/ቤቱ ቫትና ዊዝሆልድ ይቆርጣል::
 18. ተጫራቾች የአሸነፏቸዉን እቃዎች ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ሁኖ ደ/ታቦር ሆስፒታል ድረስ በራሱ ወጭ ሸፍነው ማቅረብ አለባቸዉ::
 19. ለበለጠ መረጃ ከግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስ.ቁጥር 0584411657 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡
 20. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ::

የደብረታቦር ጠቅላላ ሆስፒታል