Debere Berhan Comprehensive Specialized Hospital

Addis Zemen Tahsas 24, 2013

 

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የደብረብርሃን ኮም/እስፔ/ሆስፒታል 2013 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ የሚውል

 1. የጽሕፈት መሳሪያ
 2. የፅዳት እቃ
 3. የህሙማን እና የሠራተኞች አልባሳት
 4. የህከምና መሳሪያ መለዋወጫ እቃዎች
 5. የተለያዩ ህትመቶች
 6. የመብራት፣ የውሃና የሕንፃ መለዋወጫ እቃዎች
 7. የቢሮ መገልገያ እቃዎች/ፈርኒቸሮች
 8. ኤሌክትሮኒክስ ቋሚ እቃዎች
 9. የመኪና ጎማ ፣ ከነመዳሪና የመኪና ጌጣጌጥ እቃዎች
 10. የህሙማን ኦክሲጅን ሲሊንደር ሙሊት ከነትራንስፖርቱ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት

 • በዘመኑ (2013 በጀት ዓመት ) የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች መሳተፍ ይችላሉ፡፡
 • የግዥ መጠኑ 200.000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
 • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳን እቃ ግዥ (ሎት) ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል ከሆስፒታሉ የዕለት ገንዘብ ቤት መግዛት ይችላሉ ፡፡
 • ተጫራቾች ለሚሳተፉበት ጨረታ ሕጋዊና ተቀባይነት እና አግባብነት ያለው ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው::
 • ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦርጅናሉንና ኮፒ በጥንቃቄ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የእቃ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል ፡፡
 • ተጫራቾች በሆስፒታሉ በቀረቡት በእያንዳንዱ እቃ ዓይነትና የሥራ ዝርዝር መሠረት የጨረታ ሰነዱን ዋጋ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው ::
 • ሁሉም ተጫራቾች በያንዳንዱ የሥራ ዝርዝር እና የተጫራቾች መመሪያ መሰረት የመፈፀም ግዴታ አለባቸው ::
 • ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ጨረታዎች በሆስፒታሉ የጨረታ ሰነድ ዓይነት እና ዝርዝር (እስፔስፊኬሽን) መሠረት ማቅረብ አለባቸው፡፡
 • ተጫራቾች የሚያቀርቡትን እቃ የተመረተበትን ሀገር እና ብራንድ በጨረታ ሰነዱ ላይ መጥቀስ አለባቸው::
 • ተጫራቾች የሚያቀርቡት እቃ ጥራት ያለው እና አንደኛ ደረጃ ሆኖ በገበያ ላይ ተመራጭ መሆን አለበት፡፡
 • ተጫራቾች የውሃና የመብራት እቃዎች ሰነድ ላይ በእያንዳንዳቸው የሚያቀርቡትን ዓይነት ናሙና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው:: ናሙናዎቹን ሆስፒታሉ እየፈረመ ይረከባል አሸናፊ/ከተለየ በኋላ ተመላሽ ይደረጋሉ፡፡
 • ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ ከማቅረባቸው በፊት ናሙና በማቅረብ ትክክለኛነቱ ከተረጋገጠ በኋላ በራሳቸው ወጪ በማቅረብ ለሆስፒታሉ ንብረት ከፍል ማስረከብ አለባቸው፡፡ ሆስፒታሉ የእቃውን ጥራት እና በናሙናው መሰረት የቀረበ መሆኑን በሚመለከታቸው ባለሙያዎችና ኃላፊዎች በማረጋገጥ ይረከባል፡፡
 • ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ሁሉንም እቃዎች ዋጋ ከመሙላታቸው በፊት ሆስፒታሉ የመረጠውን ናሙና ማየትና መሙላት አለባቸው፡፡ በተመረጡት ናሙናዎች ዓይነት በዋጋ ያሸነፉባቸውን በትክክል በናሙናው መሰረት ማቅረብ አለባቸው::
 • ተጫራቾች በሆስፒታሉ የተመረጠ ናሙና ያላቀረበባቸውን የአልባሳት ዓይነት ከሞሉት ዋጋ ጋር ናሙና አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ካላቀረቡ ሆስፒታሉ በሚመርጠው ናሙና ተገዢ ይሆናሉ ፡፡
 • ተጫራቾች የሚታተሙ ህትመቶችን በሆስፒታሉ ናሙና መሰረት አትመው ማቅረብ አለባቸው ::
 • ከላይ የተገለፀው እንዳለ ሆኖ መዝገቦችን 200 ቅጠል በማተም 1400 ግራም ግራይ ቦርድ ቴላ ከቨር በመጠቀም መጠረዝ፣ ከመዝገብ ውጭ ያሉትን 100 ቅጠል ማተም እና መጠረዝ እና ከመድኃኒት ማዘዣ ፕሪስክሪብሽን በስተቀር ሁሉንም 60 ግራም A4 ወረቀት ማተም አለባቸው፡፡ እንዲሁም ፊት እና ጀርባ ጽሑፍ ያላቸውን በአንድ ቅጠል አስበው ዋጋ መሙላት አለባቸው፡፡ ከመዝገቦች ውጭና መዝገቦች ላይ A3:A2 የሚታተሙ ናሙናዎች ካሉ በናሙናው መሰረት በቀረበው ሳይዝ ይታተማሉ መጠኑም 60 ግራም ማነስ የለበትም፡፡
 • ተጫራቾች በጨረታ ሂደት ከአሁን በፊት ምንም ዓይነት ማስጠንቀቂያ ያልተሰጣቸው መሆን አለበት፡፡
 • ተጫራቾች በእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ ዝርዝር ላይ የቀረቡት እቃዎች በሙሉ ዋጋ መመላት አለባቸው።
 • ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ ዓይነት ባሸነፉበት ጥራትና ዋጋ ዝርዝር መሰረት ልዩነት ቢኖረው እና የጥራት ችግር ቢከሰት በራሳቸው ወጪ እንደገና የመተካት እና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው ፡፡
 • ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃ ናሙና ሳያቀርቡ ሙሉ ለሙሉ ይዘው ቢመጡና እቃው ተፈላጊ ዓይነት  ሳይሆን ሲቀር ሙሉ ለሙሉ ወዲያውኑ መልሰው በራሳቸው ወጪ ኣቅርበው በናሙናው መሰረት መሆኑ ሲረጋገጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 • በእያንዳንዱ የግዥ ዓይነት የሚሳተፉ ተጫራቶች በተጫራቾች መመሪያ ላይ የተቀመጠውን ሕግ ማክበር አለባቸው፡፡ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የተወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ ጨረታ  ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) 1% እና ካሸነፉ በኋላ ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10%  በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ሆስፒታሉ ገንዘብ ቤት ድረስ ማስያዝ አለባቸው፡፡
 • ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ 5 ቀን ውስጥ የውል ማስከበሪያ ያሸነፉባቸውን ጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ በውልና ማስረጃ ውለታ በመፈፀም ማቅረብ አለባቸው፡፡
 • ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ ቆይቶ 16ተኛው ቀን 400 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሳጥኑ ወዲያውኑ ይታሸጋል፡፡ 16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 430 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የበዓላት ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
 • የጨረታ ሰነዱ ጨረታ ከተከፈተ በኋላ 60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
 • ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግዥ /ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ድረስ አካል በመገኘት፣ በስልክ ቁጥር፡– 0116813390 ወይም በፋክስ 0116811008 ቁጥር በመላክ መጠየቅ ይቻላል፡፡
 • /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን በሙሉ የመሰረዝ መብቱ እንዲሁም ግዥውን በጥቅል ወይንም በተናጠል አወዳድሮ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።

የደብ/ብርሃን ኮም/ስፔ/ሆስፒታል