• Gondar
 • Applications have closed

Debark City Administration City Development Housing and Construction Office

Addis Zemen Tahsas 14, 2013

የፍላጎት መግለጫ ማቅረቢያ

ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በጎንደር ዞን የደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራከሽን /ቤት የመሬት ቆጠራ እና ፋይል መልሶ ማደራጀት እና የከተማ መሬት ይዞታ የማረጋገጥ (urban land holding adjudication consulting & Land inventory and file organization) የስራ አማካሪዎችን አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል ::

ስለሆነም የአማካሪነት ሙያ ያላቸው አማካሪዎች የፍላጐት መግለጫ እንዲያቀርቡ ይጋብዛል፡፡ ለፍላጎት ማቅረቢያ መነሻ ሃሳቦች የሚከተሉት ናቸው፡፡

 1. በአማካሪዎች እንዲሞላ የሚጠበቀው የሚፈለገው የምክር አገልግሎት፡የመሬት ቆጠራ እና ፋይል መልሶ ማደራጀት እና የከተማ መሬት ይዞታ የማረጋገጥ (urban land holding adjudication consulting & Land inventory and file organization) ተጫራቶች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የሥራ ፈቃድ ሊኖራቸው ይገባል፡፡
 2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 3. ተጫራቾች የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት /Tin Number/ ማቅረብ የሚችል፡፡
 4. ተጫራቾች በዘርፉ የሠሩ መሆኑን በተለይም በመሬት እና መሠረተ ልማት ሀብት ቆጠራ ላይ የሠሩና መረጃ የመልካም ሥራ አፈጻጸም/ ማቅረብ መቻል ይኖርባቸዋል፡፡
 5. በዚህ ሥራ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎችን ማሠማራት እንደሚችሉ እና ለዚህም የትምህርት ማስረጃ ማያያዝ የሚችሉ፡፡
 6. በአማካሪዎቹ እንዲከናወን የሚፈለጉ ዋና ዋና ተግባራት፡
  • ተማው መዋቅራዊ ፕላን (Master Plan) በከተማው የአስተዳደር ወሰን የተካለለውን እንዲሁም በገጠር ቀበሌዎች ለማኅበር የተላለፉ ቦታዎችን ጨምሮ ያለውን መሬት በቀበሌ በሠፈር፣ በብሎክና በፓርስል መለየት፣ በቋሚነትና በጊዜያዊነት የተላለፉ ይዞታዎች በአገልግሎት ዓይነትና በመሬት አጠቃቀም ፕላን፣ ቦታው መቼ እንደተገኘ በዓመተ ምህረት በባለ ይዞታ ስም፣ የይዞታ ስፋት እና እቅጣጫ ይዞታው የተያዘበት አግባብ፣ ግብር የከፈሉና ያልከፈሉ፣ ክፍት ቦታዎች በመሬት አጠቃቀም ፕላን መለየት፣ ለእያንዳንዱ ይዞታ መለያ ቁጥር (UPIC) እንዲኖረው ማድረግና የይዞታዎች መረጃ GIS (Spatial linked with non-Spatial) የይዞታ ፋይሎች በስታንደርዱ መሠረት ተደራጅተው ለአገልግሎት ምቹ እንዲሆኑ ማድረግ፡፡
  • የመሬት ቆጠራና የፋይል ማደራጀት በተጠናቀቀበት ቀበሌ 2/ሁለት/ ሠፈሮችን በመምረጥ 400 አራት መቶ/ ፋይሎችን በመመሪያው መሠረት የማረጋገጥ ሥራ መሥራት
  • በከተማው ውስጥ በሚገኘው የይዞታ ማህደር መረጃ እና ዝርዝር ሰነዶች ብዛት በመዝገቡ ለይቶ ማሳወቅ፣ በከተማው የይዞታ ማህደር ወጥነት ባለው ኮድ እና መለያ በመስጠት በቀበሌ በቀጠና በሠፈርና በብሎክ በአዲስ መልክ በመስጠት ማደራጀት፣ የይዞታ ማህደሩን ስካን በማድረግ ማስረከብ፣ የይዞታ ማህደር ጠቅላላ ቆጠራ ማከናወን ነባሩን የይዞታ ማህደር እና አቃፊ በኮድ በአዲስ መቀየር፣ የይዞታ ማህደሮች በተዘጋጀው የሸልፍ ካቤኔት ላይ በተገቢው መንገድ መደርደር/ ማስቀመጥ
 7. ማንኛውም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ አማካሪ ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ የሚሰጡትን አገልግሎቶችና የሙያ ዘርፍ አጠቃሎ የያዘ ራሪ ጽሑፍ፣ የተመሳሳይ ሥራዎች ክንውን ዝርዝር፣ የአስተዳደር አቅምና የገንዘብ አቅም ፣የአሠራር ዘዴና ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን የያዘ የፍላጐት መግለጫ እና የፋይናንስ መወዳደሪያ ሰነድ ለየብቻ በሁለት ፖስታ በማሸግ ኦርጅናልና ኮፒ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስታወቂያው በዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 13 14/4/2013 . እስከ 4/5/2013 ዓ.ም እስከ ቀኑ 1130 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን በብር 100/ አንድ መቶ ብር/ መግዛት ይቻላል፡፡
 8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 24,000 በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ በመሂ የተቆረጠ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
 9.  የፍላጐት ማቅረቢያውና የፋይናንስ ማቅረቢያው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን /ቤት ቢሮ ቁጥር 13 የጨረታ ሰነዱን እስከ 5/5/2013 . እስከ ከጠዋቱ 400 ሰዓት ድረስ ወይም ከዚያ በፊት አንድ ኦርጅናልና አንድ ፎቶ ኮፒ በታሸገ ፖስታ የፋይናንስ የቴክኒክ መወዳደሪያ ለየብቻ ከጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 10. ጨረታው ቢሮ ቁጥር 13 በተገለጸው ቦታ 5/5/2013 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 430 ሰዓት ይከፈታል፡፡
 11. የፍላጎት ሀሳብ ማቅረቢያ ለማቅረብ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በደባርቅ ከተማ አስተዳደር ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን /ቤት ቤት ቁጥር 13 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0581170033 ወይም 0581171208 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
 12. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ