SNNPR Government Office for Peace and Security

Addis Zemen Yekatit 1, 2013

የጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ/ብ/ብ/ሕ ክልል መንግስት የሠላምና ፀጥታ ቢሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችና አገልግሎቶች ማለትም

 • የደንብ ልብስ
 • የጽ/መሳሪያዎች
 • የፅዳት እቃዎች፣
 • የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
 • የሞተር ሳይክሎች፣
 • አመታዊ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ግዥና
 • አመታዊ የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባቸው:

 1. በዘመኑ ተጫራቾች ሥራውን ለማከናወን የሚያስችል የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው በአገሪቱና በክልሉ የግብር ሕጎች በተደነገገው መሠረት የግብርና የታክስ ግዴታቸውን የተወጡ፡፡
 2.  የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸውና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
 3. ለተሽከርካሪ ጥገና ጨረታ የሚሳተፉ ድርጅቶች ከደቡብ ክልል ወይም ከሲዳማ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ገበያ ልማት ቢሮ የ3ኛ ደረጃ እና ከዚያ በላይ የብቃት ማረጋገጫ የተሰጣቸው እንዲሁም ከመንገድና ልማት ትራንስፖርት ቢሮ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
 4. ለዘመኑ የታደሰ የመድህን ዋስትና ኢንሹራንስ ያላቸው፡፡
 5. ተጫራቾች በየሎቱ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50 /ሃምሣ ብር/ በመክፈል ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
 6. ተጫራቾች በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት እቃ ጠቅላላ ዋጋ 2% እንዲሁም ለተሽከርካሪ ጥገና የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (ጥሬ ገንዘብ) በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ስም አዘጋጅተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 7. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ዋናውን እና ኮፒውን ስልጣን ባለው አካል ተፈርሞና ማህተም ተደርጎ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 8. ጨረታው በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡ ሆኖም 16ተኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን የተጫራቾች ወይም ወኪሎች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም::
 9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ማካተት አለማካተቱን መግለጽ ይኖርባቸዋል፣ ሆኖም ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ቫትን ስለማካተት አለማካተቱ በግልፅ ያልተመለከቱ ከሆነ የቀረበው ዋጋ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
 10. ከተሽከርካሪ ጥገና ተጫራቾች ውጪ ያሉና የጨረታው አሸናፊ መሆናቸው የተገለጸላቸው ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ ባሉት 7 ቀናት ውስጥ ውለታውን በመውሰድ የውለታ ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 11. የእቃ አቅራቢ አሸናፊ ድርጅቶች እንደ አስፈላጊነቱ ውል ከመውሰዳቸው በፊት መ/ቤቱ የጠየቀውን የእቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
 12. ተጫራቾች የሚሞሉት የእቃ ዋጋ ላይ መለኪያና ጥራቱን ጠብቀው መሙላትና ማቅረብ አለባቸው::
 13. በመንግሥት ግዥ እንዳይሳተፍ ታግዶ የነበረ ከሆነ የዕገዳ ጊዜውን ያጠናቀቀ፡፡
 14.  በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከወጣው ጨረታ ውስጥ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ) እና ዚያ በላይ ዋጋ ባለው ግዥ የሚሳተፍ ማንኛውም የአገር ውስጥ ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት፡፡
 15. የእቃ ግዥ ጨረታ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ተገልጾ በሚሰጠው የእቃ ግዥ ትዕዛዝ መሰረት እቃዎቹን በራሱ ወጪ እስከ መ/ቤቱ የእቃ ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡
 16.  የተሽከርካሪ ጥገና ጨረታ አሸናፊ መሆኑ የተገለጸለት ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀለት በኋላ ባሉት 7 ቀናት ውስጥ ውለታውን በመውሰድ የውል ማስከበሪያ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በመያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ለአንድ አመት የሚቆይ ውል መፈራረም አለበት፡፡ ውሉን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ባይገባ ባይፈጽም የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ዋስትና ለመንግስት ገቢ ያሆናል ::
 17.  ተጫራቾች የፋይናንሻልና የቴክኒክ መገምገሚያ መስፈርቶችን በመሙላትና በተለያዩ ሁለት ፖስታዎች በማሸግ በፖስታው ላይ የፋይናንስና የቴክኒክ መሆኑን በመግለጽ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 18. ለጨረታው የውል ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ አሸናፊው ተጫራች ግዴታውን በውሉ መሰረት ካልፈጸመ በውሉ ላይ በሚገለጸው ህግ መሰረት መ/ቤቱ ተፈፃሚ የማድረግ መብት አለው፡፡
 19. ተጫራቾች ለሚጠገኑ ተሽከርካሪዎች የሚያቀርቡት ለእያንዳንዱ ስራ ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡት በፋይናንሻል ጨረታ ሰነዱ ላይ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም /መሙያ ዝርዝር ውስጥ ብቻ መሆን አለበት፡፡
 20. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልፅ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ማብራሪያ ከፈለጉ በቢሮው የግዥና/ፋይ/ንብ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 046 212 40 27 ወይም 046 221 48 22 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የደቡብ/ብ/ብ/ሕ ክልል መንግስት የሠላምና ፀጥታ ቢሮ

ሀዋሳ