Wereilu Woreda Correctional Facility

Addis Zemen Tahsas 19, 2013

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

አማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደ/ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ ማረሚያ ቤት አሰ/ፅ/ቤት ለ2013 ዓ.ም የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል

 1. ለደንብ ልብስ
 2. ፅህፈት መሳሪያ
 3. ህትመት
 4. ለህግ ታራሚዎች የምግብ እህል የሚያቀርብ
 5. የማገዶ እንጨት በሜትር ኩብ
 6. የፅዳት እቃዎች
 7. አላቂ የቢሮ እቃ  
 8. የመኪና እቃ መለዋወጫ
 9. የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ
 10. የህንጻ መሳሪያ
 11. የስልጠና እቃ
 12. ቋሚ እቃ
 13. ድንጋይ እና አሸዋ
 14. የኤሌክትሪክ እቃዎች
 15. ኤሌክትሪክ የሚሰራ የወፍጮ እቃ መለዋወጫ

በአጠቃላይ ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስገባት ይፈልጋል

ስለሆነም በዘርፉ የተሰማራችሁ ነጋዴዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል ::

ስለሆነም፡

 1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነበር ያለው/ያላት
 3. የግዥ መጠን በሎት ብር 50000/ሃምሳ ሽህ ብር/እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የምትችል
 4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ስርአት ወይም በጥሬ ገንዘብ በገንዘብ ያዥ አስይዞ ደረሰኙን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው
 5. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ማስረጃዎች ፎቶኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የድርጅቱን ስም፤አድራሻ፤ ማህተም፣ ፊርማ በማድረግ በሚነበብ መልኩ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው አያይዞ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል
 6. የጨረታ ሰነዱና መረጃዉ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ የበዛበት ከሆነና ዋጋ ያልተሞላበት ክፍት ቦታ ካለው ከውድድሩ ውጪ ይሆናል
 7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩት እቃ ናሙና እንዲያቀርቡ ሲጠየቁ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል
 8. የሚገዙ እቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ /specification / ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል
 9. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል በወረኢሉ ማረሚያ ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይቻላል::
 10. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ቫትን ጨምረው መሙላት ይጠበቅባቸዋል ካልሆነ ጨረታው ውድቅ ይሆናል
 11. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን እቃ በማረሚያ ቤቱ ግቢ ውስጥ ማቅረብ ይኖርበታል::
 12. አሸናፊው ድርጅት የሚለየው በነጠላ ወይም በጥቅል የዋጋ ድምር / በሎት /መ/ቤት በመረጠው መንገድ ይሆናል
 13. አሽናፊው ድርጅት ያሸነፈውን እቃ በማረሚያ ቤቱ ግቢ ውስጥ ማቅረብ ይኖርበታል
 14. አሸናፊው ድርጅት በተጠየቀው ዝርዝር መሰረት ጥራቱን የጠበቀ እቃ ካላስረከበ ካላቀረበ በገዛ ኪሳራው እቃውን ይመልሳል
 15. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታውን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግ/ፋ/ን/ አስ/ደ/የስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ይከፈታል።16ኛው ቀን ቅዳሜእና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል ::
 16. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
 17. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0331160143 ወይም 0331160092 ደውለው መጠየቅ ይቻላል ::

በደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ማረሚያ ቤት

/ወረኢሉ/