• Amhara

Womeberma Woreda FEDB

Be'kur Yekatit 1, 2013

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአብክመ ገ.ኢ.ት ቢሮ በምዕ.ጎ.ዞን ገ.ኢ.ት.መምሪያ የወምበርማ ወረዳ ገ.ኢ.ትብብር ፅ.ቤት በ2013 በጀት ዓመት ለስራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ስራዎችን/እቃዎችን ማለትም

 • ሎት 1፡- ሲሚንቶ ፣
 • ሎት 2፡–የወንዝ ጥቁር አሸዋ ለመግዛት እንዲሁም
 • ሎት 3. ከአርባገል ቡራፈር ያለውን መንገድ ለማስገንባት የማሽነሪ ኪራይ ማለትም ግሌደር ፤እስካቫተር፤ ሮሎ፤ ሻወርትራክ እና ገልባጭ ተጫራቾችን

በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ለመከራየት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

 1.  በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ የምዝገባ የምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፤
 3. የግዥው ወይም የአገልግሎት ግዥው የብር መጠን 200 ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
 4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 በመክፈል ወም/ወ/ገ/ኢ/ት/ፅ/ቤት ማግኘት ይቻላል፡፡
 6. ተጫራቾች የግዥውን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
 7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1፡- ብር 3,000/ሶስት ሺህ ብር/ ፣ለሎት 2፡- ብር 2,000/ሁለት ሺህ/ ሎት 3. 15000/ አስራ አምስት ሺህ ብር ለወም/ወ/ገ/ኢ/ትብብር ፅ/ቤት በማለት ይህን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ/በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በመስሪያቤታችን ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን መሂ/ደረሰኝ/ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 8. ማንኛውም ተጫራች የዋጋ መሙያውን በጥንቃቄ በመሙላት በሞሉት ዋጋ ላይ የድርጅታቸውን ስም፣ፊርማ እና ማህተም በማድረግ በአንድ ወይንም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅ ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በተለያዬ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ሲፒኦውን /ጥሬገንዘብ ገቢ የተደረገበትን ኮፒ በአንድ ፖስታ በማድረግ እነዚህን ሶስት ፖስታዎች በአንድ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በፖስታው ላይ የመስሪያቤቱን እና የአቅራቢውን ስም እና አድረሻ በመፃፍ የተጫራቹን ማህተም፣ፊርማ እና አድራሻ በመፃፍወም.ወ.ገ.ኢ.ት.ጽ. ቤት ግዥ .ን.አስ.ቡድን ቢሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
 9. የጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4፡00 የጫራታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ሎት 1 በ 4፡30 ፣ሎት 2 በ5፡00 ሎት3. 5.30 ተጫራቾች በተገኙበት ጨረታው የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት የማያግደን ከመሆኑም በተጨማሪ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናል፡፡የጨረታው መክፈቻ ቀን የመንግስት የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
 10. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀ ከ5/አምስት የስራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን የሎት ጠቅላላ ዋጋ ድምር 10% በሁኔታ ላይ ባልተመሰረት የባንክ ትዕዛዝ/በሲፒኦ/ በጥሬ ገንዘብ በማሰራት ውል መያዝ አለበት፡፡
 11. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈባቸውን የሎት እቃዎች በየመ/ቤቶች ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ወጭ በማጓጓዝ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
 12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ወም/ወ/ገ/ኢ/ትብብር ፅ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳድር ቡድን ቢሮ ድረስ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0584490215 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 13. ተጫራቾች እያንዳንዱን ዋጋ ሲሞሉ ግልፅ እና ተነባቢ መሆን አለበት፡፡
 14.  አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች/አገልግሎቶች/ ሙሉ በሙሉ በውሉ መሰረት ካላስረከበ የውል ማስከበሪያው ሙሉ በሙሉ ይወረሳል፡፡
 15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የወምበርማ ወረዳ ገ.ኢ.ትብብር ፅ.ቤት