• Wollo

Wollo University Kombolcha Institute of Technology

Addis Zemen ጥቅምት24፣2013

 

የጨረታ ማስታወቂያ

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት ለመማር ማስተማር አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ግብዓቶችን በግልፅ ጨረታ ዘዴ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም፡

1.የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠንና የቢድ ቦንድ የቆይታ ጊዜ

ተ.ቁ የግዥው አይነት የጨረታ ማስከበሪያ 

(CPO)

የጨረታ ማስከበሪያ 

ዋስትና የሚቆይበት ጊዜ 

(bid security validity day) or bid performance

ምርመራ

 

1 የጀነሬተር ግዥ (ሎት-01) 150,000.00 90 ቀናት ያህል
2 አይሲቲ እቃዎች (ሎት-02) 100,000.00 90 ቀናት ያህል
3 የጫማ ግዥ (ሎት-03) በድጋሚ የወጣ 50,000.00 90 ቀናት ያህል
4 የኤሌክትሪክ እቃዎች ግዥ (ሎት-04) 100,000.00 90 ቀናት ያህል
5 የውሃ እቃዎች ግዥ (ሎት-05) 100,000.00 90 ቀናት ያህል
6 የጣውላ ግዥ (ሎት-06) 80,000.00 90 ቀናት ያህል
7 የተለያዩ የወርክ ሾፕ እቃዎች ግዥ (ሎት-07) 100,000.00 90 ቀናት ያህል
8 ህትመት ስራዎች (ሎት-08) በድጋሚ የወጣ 50,000.00 90 ቀናት ያህል
9 የቅመማ ቅመም ግዥ (ሎት-09) በድጋሚ የወጣ 50,000.00 90 ቀናት ያህል
10 የእንጀራ መጋገር አገልግሎት ግዥ (ሎት-10) በድጋሚ የወጣ 50,000.00 90 ቀናት ያህል
11 የግቢ ውበት መገልገያ እቃዎች (ሎት-11) 50,000.00

 

90 ቀናት ያህል

 

12 የተለያየ ጨርቃ ጨርቅ እና የተለያዩ ክሮች 80,000.00

 

90 ቀናት ያህል

 

13 ቴክስታይል፣ ፋሽን እና ቆዳ ውጤቶች ግዥ

(ሎት-13) የቆዳ፣

የጨርቃጨርቅ መስሪያ ማሽኖች -13A

የቆዳ ውጤቶች ሎት-13B

100,000.00

 

90 ቀናት ያህል

 

14 የወለል ምንጣፍ (ሎት-14)

 

50,000.00

 

90 ቀናት ያህል

 

15 የማባዣ ቀለሞች (ሎት-15)

 

80,000.00

 

90 ቀናት ያህል

 

16 የፅዳት እቃዎች (ሎት-16)

 

50,000.00

 

90 ቀናት ያህል

 

17 የፕላስቲክ ወንበር (ሎት-17) 80,000.00

 

90 ቀናት ያህል

 

18 የስፖርት እቃዎች (ሎት-18) 80,000.00 90 ቀናት ያህል
19 የእስቴሽነሪ እቃዎች (ሎት-19) 50,000.00

 

90 ቀናት ያህል
20 የፈርኒቸር ግዥ (ሎት-20) የፈርኒቸር አቅርቦት

(ሎት-20A)የፈርኒቸር ስራዎች (ሎት-20B)

80,000.00

 

90 ቀናት ያህል
21 የብረታ-ብረት እቃዎች (ሎት-21 ) 80,000.00 90 ቀናት ያህል
22 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች (ሎት-22) በድጋሚ የወጣ 100,000.00

 

 

90 ቀናት ያህል

በመሆኑም፡

 1. ተጫራቾች ከሎት-1 እስከ ሎት-2 አቅርቦት ላይ ለመጫረት ተጫራቾች ለእያንዳንዱየማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈልይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ያህል ሰነዱን ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 302 በሚገኘው መውሰድ/መግዛት/ የሚችሉና ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ፖስታውን ከሁለት ኮፒ ጋር (ፋይናንሽያል ኮፒና ኦርጅናል እንዲሁም ቴክኒካል ኮፒና ኦርጂናል) ለየብቻ በማሸግ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
 2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከሎት-3 እስከ ሎት-22 ላሉት አቅርቦቶች ለእያንዳንዱየማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈልይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ያህል ሰነዱን ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግዥ ቡድን ቢሮቁጥር 302 በሚገኘው መውሰድ/መግዛት/ የሚችሉና ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ፖስታውን ከአንድ ኮፒ ጋር እንዲሁም ለየብቻ በማሸግ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
 3. ተጫራቾች ከላይ ከሚያቀርቡ እቃ ጋር ወይንም ሊሰራ ከሚፈለገው ስራ ጋር በዘርፉ ቀጥተኛ እና በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የግብር ክሊራንስ (ጨረታ እንዲሳተፉ የሚል) ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገፅ በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው::
 4. ተጫራቾች ዋጋ መሙላት ያለባቸው ዩኒቨርሲቲው ባቀረበው የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ነው። እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

6.ለሁለም ሎት ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ በጨረታው ለተሸነፈ ድርጅት አሸናፊው ድርጅት ከአዋርድ ከተደረገ በኋላ ወዲያውኑ ይመለሳል።

 1. ተጫራቾች በቀረበው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ወይንም መሠረት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
 2. አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
 3. ተጫራቾች ከሎት-1 እስከ ሎት -11 ያሉት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮበ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸግ ሆኖ በእለቱ ከጠዋቱ 4፡30የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮምቦልቻ በሚገኘው የኢንስቲትዩቱ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 302 የሚከፈት ይሆናል።
 4. ተጫራቾችከሎት-12 እስከ ሎት-22 ያሉት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓትየጨረታ ሳጥኑ የሚታሸግ ሆኖ መክፈቻ ቀኑ በማግስቱ ወይንም በ17ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው/በተገኙበት በኮምቦልቻ በሚገኘው የኢንስቲትዩቱ ግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 302 የሚከፈት ይሆናል።
 5. ተጫራቾች የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በተራ ቁጥር 9 እና ተቁ 10 መሰረት እንደቅደም ተከተላቸው በቀጣይ ቀን ባለው የስራ ቀን እና ከላይ በተጠቀሰው የስራ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።
 6. የሎት-13 እና ለሎት-20 ተጫራቾች በንኡስ ሎት ለተገለፁት ለእያንዳንዱ (A and B) የጨረታ ሎቶች ለመወዳደር ለስራው የሚቀርበው ዝርዝር የጨረታ ዶክመንት ከላይ በተራ ቁጥር 4 ላይ የተገለፀውን ዝርዝር መስፈርት መሰረት ማሟላት አለበት።
 7. የተጫራች አለመኖር ፖስታው ተሟልቶ እስከተገኘ ድረስ ጨረታውን አያስተጓጉልም።
 8. ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በመሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
 9. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ቀን ጊዜ 60 ቀናት ያህል ይሆናል።
 10. ተጫራቾች የአሸነፉትን እቃዎች በራሳቸው ወጭ እና ትራንስፖርት አጓጉዘው ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከአዘጋጀው ቦታ ድረስ በማቅረብ ማስረከብ አለባቸው::

17.ተጫራቾች ከዚህ የጨረታ ማስታወቂያ በተጨማሪ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የተያያዘውን የተጫራቾች መመሪያ እና የመደበኛ የጨረታ ሰነድ ባለማንበብ እና ባለመገንዘብ ባለመረዳት ለሚከሰተው ችግር ዩኒቨርሲቲው ተጠያቂ አይሆንም።

 1. ተጫራቾች ከዚህ በፊት ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ሆነ ከሌሎች መስሪያ ቤቶች ጨረታ አሸንፈው የአፈፃፀም ችግር የአለባቸው ወይንም ጨረታውን አሸንፈው እና ውለታ ወስደው ግንባታውን ወይንም የእቃ አቅርቦትን በውለታው መሰረት ሰርተው ያላጠናቀቁ ተጫራቾች በጨረታው የማይሳተፉ መሆኑን እንገልፃለን።
 2. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር፡- 033 851 41 20 / 0338 51 90 42/ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የወሎ ዩኒቨርሲቲ የኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት