• Pending
 • Applications have closed

Weldiya University

Addis Zemen ሰኔ20፣2012

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር ወዩ/ግ/ጨ/ቁ/ 04/2012 

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ በ2013 ዓ.ም በሚፈቀድ መደበኛና ካፒታል በጀት ለዩኒቨርሲቲው ለመደበኛ ተማሪዎች ለምግብ ማብሰያ አገልግሎት የሚውሉ የማገዶ እንጨት በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ተጫራቾች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ዩኒቨርሲቲው የሚገዛቸው እቃዎች ከዚህ በታች በሎት ተዘርዝረው ቀርበዋል ፡፡ 

 1. ሎት አንድ የማገዶ እንጨት ሲሆን በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ:: በመሆኑም ተጫራቾች፣ 

1. በስራ ዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉ፤ የግብር ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የድጋፍ ደብዳቤ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ በመንግስት ግዥና ንብ/አስተዳደር ኤጀንሲ አቅራቢዎች ዝርዝር ስለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት/ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ በማህበር የተደራጁ ከሆነ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ኃላፊ ወይም ምክትል ኃላፊ ብቻ የተፈረመ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡በባለሙያ የተፈረመ ደብዳቤ ተቀባይነት የለውም፡፡ 

 1.  ተጫራቾች ሁሉንም ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ዝርዝር የእቃ ስፔስፊኬሽን ፤ የንግድ ስራ ፈቃድ ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፧ የባንክ ሂሳብ ቁጥር፤ የዋስትና ደብዳቤ ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንት ፤ ቃሉ መሃላና የመሳሰሉ ሰነዶች ኦርጅናል ዶክመንት መታሸግ አለባቸው :: 
 2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በብር 100.00/ አንድ መቶ ብር / እንዲሁም በማህበር የተደራጁ ከሆኑ ህጋዊ ማስረጃ በማቅረብ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ጀነቶበር ዋናው ግቢ ፋይናንስና በጀት አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 07 መግዛት የሚችሉ ሲሆን በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸው አካል ማስረጃ በማምጣት የጨረታ ሰነዱን በነጻ መውሰድ ይችላሉ፡፡ 
 3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.0/ አምሳ ሺህ ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ/ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቼክና ኢንሹራንስ ማቅረብ ከውድድር ውጪ ያደርጋል ::
 4. በአነስተኛ ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሰረት የተቋቋሙ አነስተኛ ጥቃቅን ተቋማት የጨረታ ማስከበሪያ በማቅረብ ምትክ ተቋሙን ካደራጀው ጥቃቅን አነስተኛ ጽ/ቤት በጽ/ቤት ኃላፊ ወይም ምክትል ኃላፊ ብቻ የተፈረመ ዋስትና ደብዳቤ ብቻ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
 5. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሳቸው ወጪ የማጓጓዝና ሌሎች የማውረጃንና የማስጫኛ የጉልበታ ዋጋ ወጪዎችን ሸፍነው ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ጀነት በር ዋናው ግቢ ንብረት ክፍል ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል ፡፡ 
 6. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 20/10/2012 ጀምሮ እስከ 5/11/2012 ዓ.ም 11፡30 ድረስ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ፋይናንስና በጀት አስ/ዳይ/መግዛት የሚችሉ ሲሆን ተጫራቶች ከ20/10/2012 እስከ 6/11/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል ፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቶችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እንዲሁም የጨረታውን ሂደት መከታተል የሚፈልጉ አካላት በተገኙበት በንግድ ማዕከሉ አዳራሽ ይከፈታል፡ : ተጫራቶችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈቱ ኦይታገድም :: 
 7. ተጫራቾች አላስፈላጊ ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የሚገቡበትን ዩኒቨርሲቲው ያቀረበውን ቅጽ ሞልተውና ፈርመው ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ለመመለስ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው፡፡
 8. ተጫራቾች ሰነዶች ገጽና በፖስታው ላይ የድርጅቱን ማህተም በማተምና በመፈረም በጥሩ አስተሻሸግ በማሸግ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል :: 
 9. ተጫራቾች የማገዶ እንጨት ጨረታው ለአንድ ዓመት የሚቆይ እና የዋጋ ማስተካከያ የማይደረግ መሆኑን አውቀው መጫረት ይጠበቅባቸዋል፡፡ 
 10. ጨረታው ከተከፈተ አንስቶ ለ90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ሲሆን ሲፒኦ ሲያሰሩ 118/ለአንድ መቶ አስራ ስምንት ቀን መሆን ይጠበቅበታል ፡፡ 
 11. ተጫራቾች ማንኛውንም መረጃ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን ፖስታው በመተለቁ ምክንያት ሳጥኑ ውስጥ መግባት የማይችል ከሆነ የጨረታ ሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት አስመዝግበው መስጠት ሲኖርባቸው የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ ማንኛውንም ማስረጃ በእጅ ይዞ መቅረብ አይቻልም ከጨረታ ውጪ ያስደርጋል፡፡ በተጨማሪም ስርዝ ድልዝ ያለበት የዋጋ መሙያ ስርዝ ድልዝ ያለበት ተራ ቁጥር ከውድድር ውጭ ስለሚሆን በጥንቃቄ መሙላት ና ስርዝ ድልዝ ካለም ፓራፍ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ 
 12. ዩኒቨርሲቲው ከሚገዛው አጠቃላይ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 033 540 2186/033 43115 44 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ የወልድያ ዩኒቨርሲቲ