• Wollo

Weldiya University

Addis Zemen Tir 28, 2013

 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ወይ/ግ/መ/ቁ/08/2013

የወልድያ ዩኒቨርሲቲ በ2013 እና በ2014 ዓ.ም ከሚፈቀድ መደበኛ እና ካፒታል በጀት ለዩኒቨርሲቲው አገልግሎት የሚውሉ የባልትና ውጤቶች፣ የፋብሪካ ውጤቶች፣ የእንስሳት ተዋጽኦ፣ የአትክልት ተዋጽኦ፣  ጤፍ፣ ጎመን ዘር፣ የዳቦ ዱቄት፣ የፅዳት እቃዎች፣ የመኪና ጎማና መለዋወጫ እቃዎች፣ የአይሲቲ ፕሮጀክት አማካሪ ድርጅቶች፣ የስፖርት እቃዎች፣ የግንባታ እቃዎች የአርማታ ብረትና ሲሚንቶ፣ ኤሌክትሮኒከስ እና የጽሕፈት መሳሪያዎች በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ ተጫራቾች መካከል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ዩኒቨርሲቲው የሚገዛቸው እቃዎች ከዚህ በታች በሱት ተዘርዝረው ቀርበዋል፡

 • ሎት 1/አንድ የባልትና ውጤቶች
 • ሎት 2ፋብሪካ ውጤቶች
 • ሎት 3/ሶስት/የእንስሳት ተዋጽኦ
 • . ሎት 4 /አራት/የአትክልት ተዋጽኦ
 • ሎት 5/ ኣምስት/-ጤፍ
 •  ሎት 6 /ስድስት/ጎመን ዘር
 • . ሎት 7 /ሰባት/-የዳቦ ዱቄት
 • . ሎት 8/ስምንት/-የጸዳት እቃዎች
 • ሎት 9/ዘጠኝ/ -የመኪና ጎማና መለዋወጫ እቃዎች
 • ሎት 10 /አስር/የስፖርት እቃዎች
 • ሎት 11/ኣስሪ እንደ/- የግንባታ እቃዎች የአርማታ ብረትና ሲሚንቶ
 • ሎት12 /አስራ ሁለት/- የኣይሲቲ ፕርጀክት አማካሪ ደርጅቶች
 • ሎት 13 /አስራ ሦስት/- -ኤሌክትሮኒክስ
 • ሎት 14 /አስራ አራት/-  የፅሕፈት መሳሪያዎች

በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተጠቀውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶች ቀርበው መወዳደር ይችላ

 1.  ተጫራቾች በየምደቡ በሥራ ዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው በአቅራቢዎች ዝርዝር፣ በመንግሥት ግዥና ንብረት እስተዳደር ኤጀንሲ ዌብ ሳያት እቃና አገሬግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉህ የተጨማሪ እሴት ታ ሪ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ በኢትየጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቀጥር ያላቸው መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ያላቸወና ያዘምኑን የሥራ ግብር የከፈሉ፣ የግብር ግዴታቸወን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የድጋፍ ደብዳቤ ካntዎች ባለሥልጣን ማቅረብ የሚችሉ፤ እንዲሁም በማህበራት የተደራጁ ከሆኑ በፕታና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ፅ/ቤት ኃላፊ ፊርማ ብቻ ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በባለሙያ የተፈረመ የድጋፍ ደብዳቤ ተቀባይነት እይኖረውም፡፡ ሁሉንም ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ እሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሆኖም ግን ቴከኒካል ላላቸው ፋይናንሽያል ጀነት mለብቻ ቴክኒካል ዶከመንት የንግድ ሥራ ፈቃድ፤ ቲን ነምበር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት፤ የድጋፍ ደብዳቤ፣ ሲፒኦና የመሳሰሉት መረጃዎች ተጨምሮ ለብቻ በጥሩ እስተሻሽግ መታሸግአለበት።
 2. ተጫራቶች ኦርጂናል ዶክመንትና ኮፒ ለየብቻ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቹን ከሎት (1) (አንድ) እስከ ሎት (14) አስራ አራት ብር 100.00(አንድ መቶ ብር) ብቻ በመከፈል እንዲሁም በማህበር የተደራጁ ከሆኑ ሕጋዊ ማስረጃ በማቅረብ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ፋይናንስና በጀት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ሙግዛት ይችላሉ፡፡
 4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ከሎት 1) (ኣንድ) እስከ ሎት (14) አስራ አራት ለእያንዳንዱ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ብቻ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) የባንከ ጋራንቲ ከቴክኒካል ዶከመንት ሰነዶች ጋር አብረው አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቼከና ኢንሹራንስ ማቅረብ እይቻልም/የተከለከለ/ ነው።
 5. በአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት አዋጅ መሠረት የተቋቋሙ አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት የጨረታ ማስከበሪያ በማቅረብ ምትከ ተቋማቱን ከአደራጀው ከጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ኢንዱስትሪ ሥራዎች ማስፋፊያ ፅ/ቤት ብቻ በፅ/ቤት ኃላፊው የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
 6. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሳቸው ወጪ የማጓጓዝና ሌሎች የማውረጃን የመጫኛ ወጪዎችን ሸፍነው የሚገጣጠሙ ካሉም በመገጣጠም ሥልጠና የሚያስፈልጋቸውንም ሥልጠና በመስጠት ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ጀነቶ በር ዋናው ግቢ እና መርሳ ግብርና ኮሌጅ ንብረት ክፍል ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል::
 7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ28/5/2013 ዓም ጀምሮ እስከ 12/6/2013 ዓም ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ፋይናንስና በጀት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡ በመሆኑም ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አስ/ር ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 15/6/2013 ዓም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን ማለትም ከሎት (እንድ) እስከ ሎት 14/ (አስራ እራት) ማስገባት ይችላል፡፡ የጨረታ ሣጥኑ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ጀምሮ በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ በንግድ ማዕከሉ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ከመከፈቱ አይታገድም፣
 8. .ሎት 12 (አስራ ሁለት) የአይሲቲ ፕሮጀክት ኣማካሪ ድርጅቶች እና ሎት13 (አስራ ሦስት) ኤሌክትሮኒክስ የቴከኒካል ኦሪጂናልና ኮፒ ፋይናንሽያል ኦሪጂናልና ኮፒ ዶክመንት ለየብቻው በማዘጋጀት ዝርዝር የእቃው ስፔስፊኬሽን /የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ ቲን ነምበር (የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር)፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት፣ የገቢዎችና ጉምሩክ ከሊራንስ የድጋፍ ደብዳቤ፣ ሲፒኦ እና፣ ቃለ መሃላ፣ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀትና በኢትዮጵ ንግድ ባንከ ሂሳብ ቁጥር እና ለአይሲቲ ፕሮጀከት አማካሪ ድርጅቶች በማማከር ሥራ ላይ የተሰጠ የድጋፍ ደብዳቤና ፈቃድ ያላቸው መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የመሳሰሉት መረጃዎች ዋናውንና ኮፒውን፤ ተጨምሮ/ለብቻ በጥሩ አስተሻሸግ በመታሸግ መቅረብ አለበት፡፡
 9. ሎት 8(ስምንት) የፅዳት እቃዎች፣ ሎት 10 (ኣስር) የስፖርት እቃዎች እና ሎት 14 (እስራ አራት) የጽሕፈት ሣሪያዎች የፋይናንሽያል ኦሪጂናልና የፋይናንሽያል ኮፒ ለየብቻ በማሸግ እና የሚያቀርበትን የእቃ ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 10. ተጫራቾች አላስፈላጊ ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የሚገቡበትን ዩኒቨርሲቲው ያቀረበውን ቅፅ ሞልተውና ፈርመወ) ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ለመመለስ ፈቃደኛ መሆን እለባቸው
 11. የቴክኒክ ግምግማውን እና የእቃናሙና የተመረጠላቸውና ያለፉ አቅራቢ ድርጅቶች ለዋጋ ውድድር የሚቀርቡ ይሆናል፡፡ በሁሉም የመወዳደሪያ ሰነዶች ገጽና በፖስታው ላይ የድርጅቱን ማህተም በማተም በመፈረም በጥሩ አስተሻሽግ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
 12. ጨረታው ከተከፈተ አንስቶ ለ90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ሲሆን (CPO) ሲፒኦ ሲያሰሩ የ118 ቀን መሆን አለበት፡፡
 13. ከሎት 1 (አንድ) እስከ ሎት 7 (ሰባት) ያሉት የምግብ ግብዓቶች የዋጋ ማሻሻያ የሚደረግላቸው ውል የወሰዱትን 10% (አስር ፐርሰንት) ከአቀረቡና ስለማቅረባቸው ከሚመለከተው ከፍል ማረጋገጫ ሲቀርብ ከማዕከላዊ እስታትስቲክስ በሚላክልን የገበያ ጥናት ከጨመረ የሚጨምር ከቀነሰ የሚቀንስ ይሆናል፡፡ ቅድሚያ ክፍያን በተመለከተ ምንም እንኳን የግዥ መመሪያው ክፍያ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን ቢገልጽም ዩኒቨርሲቲው ካለበት የበጀት እጥረት የተነሳ ቅድሚያ ክፍያ መክፈል አይቻልም:: ከሎት 8 (ስምንት) እስከ ሎት 14 (አስራ አራት) ያሎት ግብዓቶች ምንም ዓይነት የዋጋ ማሻሻያ አይደረግላቸውም፡፡
 14. . ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታክስ እንዲሁም የትራንስፖርት እና የመጫኛና ማውረጃ የጉልበት ዋጋ ጨምሮ መሙላት አለበት፤ ይህ ካልሆነ ግን ያቀረበው ዋጋ ሁሉንም ወጪ አካቶ እንደተሞላ ተደርጎ ይቆጠራል፡፡
 15. ስርዝ ድልዝ ያለበት የዋጋ መሙሊያ ስርዝ ድልዝ ያለበት ተራ ቁጥር ከውድድር ውጪ ይሆናል ::
 16. ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ

በስልክ ቁጥር፡- 033 540 21 86 /033 431 15 44 ደውሎ ጠየቅ ይቻላል፡፡

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ