• Gurage

Welkite Town First Instance Court

Addis Zemen Tir 22, 2013

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዢ ቁጥር-001/2013

በደቡብ ////መንግስት በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የህጻናት ችሎት ማለማመጃ ቀሪ ስራዎች ማለትም መፀዳጃ ቤት፣ አጥር፣ የጥበቃ ቤት ከላይ ማማ ያለው፣ የውኃ ማጠራቀሚያ መስቀያ ግንባታ ግዥ ለመፈጸም በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ስራውን ተቋራጮች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት፡

ከዚህ በታች የተገለጹት መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡

1ኛ/ ተጫራቾች በፌደራል ወይም በክልል ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ወይም በዞን ፋይናንስና ኢኮኖሚ መምሪያ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው የእውቅና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2/ ህጋዊና የታደሰ የንግድፍቃድ ማቅረብ የሚችልና የዘመኑ የስራ ግብር የከፈሉ፣ ቲን ነምበር ተመዝጋቢ የሆነ እና ማቅረብ የሚችል፡፡

3/ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን፤ 22ተኛው ቀን ከቀኑ 800 ሰዓት ታሽጎ በዛው እለት 830 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቴክኒካል ዶክመንት ይከፈታል፡፡

4ኛ/ ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ አዲስ /ክተማ ከሚገኘው የገቢዎች ቅርንጫፍ ቢሮ በመክፈልና ሪሲቱን በመያዝ ከወልቂጤ ከተማ // /ቤት ግዥ ክፍል ዘወትር በስራ ሰአት መውሰድ የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡

5ኛ/ ተጫራቾች የጨረታ ቴክኒካልና ፋይናንሽያል ዶክመንት ሲያቀርቡ ከስር በተገለጸው መሰረት ይሆናል፡፡

/ ለቴክኒካል ዶክመንት 1 ኦርጅናልና 2 ፎቶ ኮፒ ኮፒ አንድ እና ኮፒ ሁለት በማለት ለየብታቸው በማሸግ ጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00 /ሀምሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ፣ ቢድ ቦንድ ወይም ባንክ ጋራንቲ ከቴክኒካል ኦርጅናል ጋር በማድረግ በእናት ፖስታ አድርጎ በሰም በማሸግ ቴክኒካል በሚል በመለየት እና ለፋይናንሽያል ዶክመንት 1 ኦርጅናልና 2 ፎቶ ኮፒ ኮፒ አንደ እና ኮፒ ሁለት በማለት ለየብቻቸው በማሽግ በእናት ፖስታ አድርጎ በሰም በማሸግ ፋይናንሽያል በሚል በመለየት 22ተኛው ቀን ከቀኑ 800 ሰዓት ድረስ ብቻ ወልቂጤ ከተማ // /ቤት //አስ/ዋና/ስራ ሂደት ክፍል ውስጥ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን የሚገባ ሲሆን የቴክኒካል ዶክመንት ጨረታው 8:30 ሰዓት ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

6 ከቴክኒካል ግምገማ ወደ ፋይናንሽያል ያለፉ ተወዳዳሪዎች ፋይናንሽያል ዶክመንት የሚከፈትበት ቀነ ቀጠሮ በተቋሙ በማስታወቂያ ቦርድ የሚገልጽ ይሆናል፡፡

7/ BC (ቢሲ) GC (ጂሲ) ደረጃ 7 እና ከዚህ በላይ ፈቃድ ያላቸው ብቻ መወዳደር የሚችሉ መሆኑ፡፡

8 በጨረታው ለመወዳደር ለሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ህጋዊ ውክልና ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡

9ኛ/ /ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኝ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

10ኛ/ በጨረታው ሰነድ ላይ እውቅና ያልተሰጠው ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም::

ማሳሰቢያ

  1. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታ ኮሚቴ ጨረታው ሊከፍት ይችላል፡፡
  2. በአፈጻጸም ምክንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መወዳደር አይችሉም፡፡
  3. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ ወዳለው የሥራ ቀን ይዘዋወራል፡፡
  4. ተጫራቾች በመወዳደሪያ ሰነዳቸው በሁሉም ገጽ እና ፖስታ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውና ማህተም ማሳረፍ አለባቸው፡፡
  5. በጨረታው ሂደት ውስጥ ለየትኛውም ግምገማ ተሻሽሎ የወጣው የክልሉ ግዢ መመሪያ ተግባራዊ የሚደረገ መሆኑ እንገልጻልን፡፡

ለበለጠ መረጃ አድራሻ፡በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ////ቤት ብሩክ ህንጻ ፊት ለፊት ቴሌ አጠገብ ከተሰራው አዲሱ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ህንጻ ውስጥ 1 ፎቅ ወደ ቀኝ ሲታጠፉ የወ//////ቤት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0113658187 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ::

በደቡብ ////መንግስት

በጉራጌ ዞን በወልቂጤ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት