ኮልፌ አካባቢ አጫራቾች አንድነት አክስዮን ማህበር

Addis Zemen Hidar 25, 2013

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/13

የኮልፌ አካባቢ አጫራቾች አንድነት አክሲዮን ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 አስኮ ኣካባቢ ለሚያስገነባው 2B+G+8 ቅይጥ ህንጻ ዲዛይን ለማሠራት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ አማካሪዎች፡-

  1.  የዘመኑን ግብር የከፈሉና ደረጃ 3 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፣ በመስኩ የተሰማሩ ህጋዊየታደሰ የንግድስራፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪእሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት፣ የንግድ ሥራ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፍኬት እና በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ 300 ሰዓት እስከ 1000 ሰዓት ኮልፌ ቅዱስ ራጉኤል አዲስ ህይወት ኢሚ የገበያ ማዕከል 3 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1138 በአካል በመቅረብ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ እንዲሁምፋይናንሻል ኣንድ ኦርጅናል እና ኣንድ ኮፒ ለየብቻበጥንቃቄ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማዘጋጀት ከላይ በተጠቀሰው የቢሮ አድራሻ ይህ ማስታወቂያ በወጣ እስከ 9ኛው የስራ ቀን እስከ 800 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 330 ሰዓት በዝግ ይከፈታል፡፡
  4. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚደርስ ሰነድ ሳይከፈት ለተጫራቹ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
  5. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 091702175/0924438090 ደውለው ይጠይቁ፡፡
  6. ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኮልፌ አካባቢ አጫራቾች አንድነት አክስዮን ማህበር