Kembata Tembaro Zone Finance and Economic Development Bureau

Addis Zemen Hidar 10, 2013

የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

የከምባታ ጠምባሮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የዞኑ አስተዳደር በዱራሜ ከተማ የሚያስገነባውን የዞኑን ገጽታ የሚያሳይ አደባባይ ግንባታ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ አወዳድሮ ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም

  1. ደረጃቸው GC-7/BC-7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ
  2. ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና የታከስ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
  3. ተጫራቶች 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ/ የጨረታ ዋስትና በሲፒኦ /የባንክ ጋራንት/ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ በመክፈል ዘወትር በሥራ ቀናት በፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 10 ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒለየብቻቸው በማሸግና በአንድ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ጨረታው በወጣበት በ22ኛው ቀን ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ 8፡15 ማስገባት አለባቸው፡፡ ነገር ግን 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል። መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ፡-0465541393 ዱራሜ

የከምባታ ጠምባሮ ዞን ፋይናንስ

መምሪያ ግዥና ንብረት

አስተዳደር ዳይሬክቶሬት