የኦሮሚያ የእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ቢሮ

Addis Zemen መስከረም14፣2013

የጨረታ ማስታወቂያ 

ጨረታ ቁጥር 0ANRB/NCB/02/2013 

የኦሮሚያ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ የተለያዩ የፍራፍሬና የዛፍ ዘሮችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ 

በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ፡- 

  1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው መንግስታዊ ድርጅቶች የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 
  2. ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ 
  3. የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ከቄራ ወደ ሳርቤት በሚወስደው መንገድ ከስኩል ኦፍ ኔሽንስ /School of Nations/ ፊት ለፊት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር የኦሮሚያ መሥሪያ ቤቶች ሕንጻ ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው ኦሮሚያ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ የመሃሉ ብሎክ 3ኛ ፎቅ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ዘወትር በስራ ቀን ከ3፡00 ሰዓት እስከ 10፡30 ሰዓት ድረስ መገዛት ይችላሉ፡፡ 
  4. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ/ በCPO” ወይም የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በራሳቸው ሰነድ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በማድረግ ቴከኒካል እና ፋይናንሻል ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ አዘጋጅቶ በኤንቨሎፕ ማሸግና በአንድ ላይ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በጨረታ መክፈቻው ዕለት በ03/02/2013 ዓም እስከ ረፋዱ 4:30 ሰዓት ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡ 
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ03/02/2013 ዓ.ም ከረፋዱ በ5:00 ሰዓት በግልጽ ይከፈታል:: 
  7. ማንኛውም ጥያቄ ወይም ማብራሪያ የሚስተናገዱት በጽሑፍ ሲቀርቡ ብቻ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ 
  • ስልክ ቀጥር 011882-91-73 ፋክስ 011-371-7488 
  • ፖ.ሳ.ቁ 8770 

የኦሮሚያ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ