• Gondar

Injibara City Administration House & Construction Bureau

Be'kur Yekatit 1, 2013

የከተማ መሬትን በሊዝ ጨረታ ለማስተላለፍ የወጣ ማስታወቂያ

  1. የጨረታ ዙር፡ የ2013 በጀት ዓመት ሁለተኛ ዙር ጨረታ
  2. የጨረታዉ ዓይነት፡ መደበኛ ጨረታ
  3. የእ/ከ/አስ/ከ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ፅ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገዉ አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረዉ መሰረት ለመኖሪያ፣ ለድርጅት፣ ለማኒፋክቸሪንግ፣ ለመጋዘን እና ለኬጅ/ለመዋለ ህፃናት/ የተዘጋጀ ቦታን በመደበኛ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ ባለኮከብ ሆቴልና ሪዞርት የሚሆኑ ሰፋፊ ቦታዎች ተዘጋጅተዋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ማንኛዉም 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ እድሜ ያለው ኢትዮጵያዊ በጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የቦታዉን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለመኖሪያ 300 ብር፣ ለድርጅት፣ ለማኒፋክቸሪግ/ለመጋዘን/ 500 ብር በመክፈል በእን/ከ/አስ/ከልቤኮ/አገ/ፅ/ቤት ከ/መ/ል/ባ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 04 ዘወትር በስራ ቀን እስከ 11፡00 መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናስታወቃለን፡፡
  4. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ሰነዱን ከገዙበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚዘጋበት ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ከቀኑ እስከ 11፡30 ብቻ ይሆናል፡፡
  5. ጨረታዉ የሚዘጋዉ ሰነድ ሽያጭ ባለቀበት ቀን ከቀኑ 11፡00 ይሆናል፡፡
  6. ለጨረታ የቀረቡ ቦታዎችን ማስታወቂያው በአየር ላይ ከዋለ በኋላ ከተቋሙ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚወጣው ፕሮግራም መሰረት ከባለሙያ ጋር መጐብኘት ይችላሉ፡፡
  7. ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው ከታሸገበት በቀጣዩ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 የመኖሪያ በቀጠዬ ቀን የድርጅች፣ የማኒፋክቸሪንግ/መጋዝን / እና በእን/ከ/አስተዳደር አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  8. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከተቋሙ የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. መስሪያ ቤቱ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ ስልክ ቁጥር፡ (251)058 827 90 34 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የእንጅባራ ከተማ አስተዳድር ከልቤኮ/አገ/ ፅ/ቤት