Injebara Teachers Education College

Be'kur Tir 17, 2013

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የእንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በኮሌጁ ግቢ ውስጥ ያሉውን የመማሪያ ክፍል ህንፃ ብሎክ ሁለት

 • ሎት 2 /በድጋሜ/ ጥገና እና እድሳት ለማሰራት GC & BC ደረጃ 7 እና በላይ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾችን፣
 • ሎት 3፡-የተለያዩ የተዘጋጁ ልብሶችና ጫማዎችን
 • ሎት 1፡-ብትን ጨርቅን በግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለማስጠገን፣ ለማሳደስና ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ

በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠየቁትን ግዴታዎች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

 1.  ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
 2. የግዥ መጠን ብር 200 ሺህ እና በላይ ከሆነ አቅራቢዎች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የቫት ተመዝጋቢ መሆንዎን የሚገልጽ ማስረጃ እና እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 3. እንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ባዘጋጀው የጨረታ መመሪያና እስፔስፊኬሽን መሰረት መጠገን፣ማደስ እና ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ስለዚህ የደንብ ልብሶችን ዓይነት በተመለከተ ኮሌጁ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት ማቅረብ የሚችሉ/በጨረታ መክፈቻ ቀን የሞላችሁትን የደንብ ልብስ ዓይነት ናሙና ይዞ መቅረብ /ይኖርባቸዋል፡፡ ምክንያቱም የተሞላውን የደንብ ልብስ ዓይነት ናሙና ይዞ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ድርጅት ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
 4. በሁሉም ሎት አሸናፊው ተጫራች የሚመረጠው በሞላው ጠቅላላ ዝቅተኛ የአንዱ /ጥቅል/ ዋጋ ይሆናል፡፡ ስለዚህ የእያንዳንዱ ሎት የአንዱን ዋጋ ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ሙሉ በሙሉ ከጨራታው ውጭ ይደረጋሉ፡፡
 5. የህንፃ ጥገና እና እድሳት ለማድረግ በጋዜጣ ህዳር 7/2013 ዓ.ም በ26ኛ ዓመት ቁጥር 49 በወጣው ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ላይ ተወዳድረው አሸናፊ ከሆኑ በኋላ ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ያልሆኑት እና አሸናፊ ሆነው ውል በመያዝ ላይ የሚገኙት ለስራው ጥራት እና የዕድሳቱ ስራ ለመማር ማስተማሩ ስራ በወቅቱ እንዲጠናቀቅ ስለሚፈለግ መወዳደር አይችሉም፡፡ በመሆኑም በኮሌጁ በጥገና እና እድሳቱ አሸናፊ ሆነው ውል በመያዝ ላይ ያሉ እና አሸንፈው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ያልሆኑት ተወዳድረው የተገኙ ተጫራቾች ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
 6. የጥገና እና እድሳት የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 07/06/2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ መግዛት የሚችሉ ሲሆን፤ የደንብ ልብስን በተመለከተ ሰነድ የሚገዙበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 01/06/2013 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ በመግዛት፤ የሚሸጡበትን ዋጋ በተዘጋጀዉ ቅፅ ሞልተው ከተጠየቁት ማስረጃዎች ጋር የጨረታ ሰነዱን እና የጨራታ ማስከበሪያውን ቢድ ቦንድ የጠቅላላ ዋጋውን 2 በመቶ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተመሰከረለት ቼክ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ የምታሲዙ ከሆነ በኮሌጁ ገቢ ደረሰኝ ገቢ አድርጋችሁ የደረሰኙን ኮፒ ከሰነዳችሁ ጋር አያይዛችሁ፤ አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ከቀን 17/05/2013 ዓ.ም እስከ 02/06/2013 ዓ.ም /የደንብ ልብስ/ እና 17/05/2013 ዓ.ም እስከ 08/06/2013 ዓ.ም /ጥገና እና እድሳት/ 3፡45 ድረስ እንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግዥ፣ፋይናንስና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 7. ተጫራቾች ከአሁን በፊት በመንግስት ግዥ ላይ ተሳትፈው በውለታችሁ መሰረት ባለመፈፀማቸዉ ምክንያት ስልጣን ባለው አካል እገዳ ያልተደረገባችሁ መሆን አለበት፡፡
 8. ጨረታ ሳጥኑን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀን 02/06/2013 ዓ.ም /የደንብ ልብስ/ እና 08/06/2013 ዓ.ም /ጥገና እና እድሳት/ ከጠዋቱ 3፡45 ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡00 ይከፈታል፤ ተጫራቾች በመክፈቻዉ ዕለት ባይገኙም ጨረታው በሰዓቱ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 16ኛው እና 22ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡
 9. አሸናፊ የሆነ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መፈፀም ይኖርባቸዋል፡፡
 10. ግዥ ፈጸሚ አካላት አሸናፊው ተጫራች የሚጠግነውንና የሚያድሰውን መጠን ወይም ብዛት 20 በመቶ መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል፡፡
 11. እንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
 12. ተጨራቾች ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ጉዳዮች በግዥ አፈፃፀም መመሪያው ቁጥር 1/2003 መሰረት ተገዢ ይሆናሉ፡፡ ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ -0588279045 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የእንጅባራ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ