Ethiopian Agricultural corporation

Addis Zemen Tir 25, 2013

የምጥን ማዳበሪያ ግብአቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ 

የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች ኣቅርቦት ዘርፍ

 • ሎት1 የኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ፖታሲየም / ዚንክ / ቦሮን ማዳበሪያ (አዲስ አበባ፣ አዳማ ሞጆ፣ አምቦ፣ አሰላና ኢተያ)
 • ሎት 2 መቀሌ እንደርታ ዩኒየን፣
 • ሎት 3 ባህር ዳር መርከብ ዩኒየን፣
 • ሎት 4 ቱሉ ቦሎ ስቶ ወሊሶ ዩኒየን፣
 • ሎት 5 ነቀምት ጊቤ ዴዴሳ ዩኒየን፣
 • ሎት 6 ወራቤ እና ቡታጅራ መሊቅ ዩኒየን የሚገኝ ፖታሽ/MOP፣ ቦሮን እና ዚንክ እንዲሁም ፈረቲኮት ባሉበት ሁኔታ በማየት መግዛት ለሚፈልጉ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተጫራቾች ማሟላት ያስባቸው ግዴታዎችና የመወዳደሪያ መስፈርት

 1. የብቃት ማጋገጫና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒውን ከዋናው ጋር እንዲመሳከር ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው ።
 2. በማዳበሪያ ሴክተር ተገቢው አቅም እውቀትና ልምድ ያለው ተቋም ወይም ድርጅት ለዚህም Company profile ማቅረብ አለባቸው፡፡
 3. ማዳበሪያዎቹንና የማዳበሪያ ግብዓቶችን በምጥን ማዳበሪያነት አቀነባብረው ለሚያመርቱ ወይም እሴት በመጨመር ለግብርና ልማት ጥቅም ላይ ማዋል ለሚችሉ ቅድሚያ ይሰጣል።
 4. ሁሉንም ማዳበሪያዎችና የማዳበሪያ ጥሬ እቃዎች በአንድነት ለመግዛትና ለማንሳት  የሚችሉ ገዥዎች ቅድሚያ ይሰጣል፡፡
 5. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለጸበት በ15 ቀናት ውስጥ እስፈላጊውን ፎርማሊቲ አሟልቶ ውለታ መፈጸምና በዘጠና ቀናት ውስጥ ከመጋዘኖቹ፣ ግብዓቶቹን ማንሳት ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቱን አጠቃሎ ካላነሳ ለዘገየበት ለቆየበት የመጋዘን ኪራይ በየቀኑ በአንድ ኩ/ል 0.25 ሳንቲም ሂሳብ ይከፍላል፡፡
 6. አሸናፊ ድርጅቱ የግብርና ሚ/ር ለሚያደርገው የድህረ ሽያጭ ክትትልና ድጋፍ: ፈቃደኛ መሆን ይኖርበታል ፡፡
 7. ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ወይም ተቋም ጨረታውን ማሸነፉ በተገለፀለት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ክፍያውን በሙሉ አጠናቆ መከፈል ይኖርበታል።
 8. ማንኛውም ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንዲሆን የመግዥያውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ አለባቸው ።
 9. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርባቸው መረጃዎች ስርዝ ድልዝ የሌለባቸውና ትክክለኛ መሆን አለባቸው የተጭበረበረ ሰነድ ማቅረብ ከውድድር ውጪ ያደርጋል፡፡
 10. በጨረታ ተሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት ገንዘብ ወይም ሲፒኦ ጨረታው ተጠናቆ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ ይሆናል።
 11. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ለመወዳደር የማይመለስ ብር 300.00 በመከፈል ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድና የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም በመውሰድ በየሎቱ ማቅረብ ይኖርበታል።
 12. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን እስከ Yekatit 11 ቀን 2013 ዓም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
 13. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ማዳበሪያ ወይም ፈርቲኮት በኩ/ል ወይም በሊትር እያንዳንዱን አይነት የሚገዙበትን ዋጋ በመጥቀስ በጨረታ ሰነዱ ላይ በቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ መሠረት በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎኘ ማቅረብ አለባቸው፡፡ በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ መሠረት ሞልቶ የማያቀርብ ተጫራች ሰነዱ ተቀባይነት የለውም፡፡
 14. ጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት Yekatit 11 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ከአቃቂ ክፍለ ከተማ ከቃሊቲ ጉምሩክ ፊት ለፊት ወደ ቅመማ ቅመም ፋብሪካ በሚያስገባው መንገድ በሚገኘው የዘርፉ ፅ/ቤት አንደኛ ፎቅ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
 15. ዘርፉ ስለ ግብዓቶቹ አሻሻጥ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
 16. ተጫራቾች ግብዓቶችን መመልከት ከፈለጉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ግብዓቶቹ በሚገኙባቸው መጋዘኖች በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
 17. ለተጨማሪ መረጃ የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ፡ በቀጥታ መስመር
 • ስልክ ቁጥር 0114425623/011442560 ደውሎ ማግኘት ይቻላል፡፡

በኢፌዴሪ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ

የኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን