የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

የጨረታ ቁጥር SS NT-T191

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ማንኛዉንም GC/BC 6 እና ከዚያ በታች የሆኑ ኮንትራክተሮችን እና አነስተኛ እና ጥቃቅን የድርጅት ተቋራጮች በንግድ ቢሮ ሚኒስትር የተረጋገጠ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ እንዲሁም ከታች የተዘረዘሩትን ስራዎችን እና መስፈርቶች የሚያሟሉ  ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በኮንትራት ለማሰራት ይፈልጋል:: ፕሮጀክቱ የሚከተሉትን ሥራዎችን ያካትታል፡፡

 • Electrical and Sanitary works
 • Metal and welding works
 • Civil works (including masonry works, carpentry works, painting…)
 • Steam and laundry system maintenance work
 • Machine erection works
 • Installation of air condition unit and repair
 • Installation of ventilation system and duct works
 • Other related worksስለሆነም በሙያው ዘርፍ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የምዝገባ ወረቀት ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ተጫራቾች ፡ እንዲሁም ብር 1,000,000 እና ከዚያበላይ በሆነ ዋጋ ቢያንስ ሁለት(2) ፕሮጀክቶችን በተሳካ ሁኔታ ያጠናቀቁና በሙያዉ  ቢያንስ ሶስት (3)  ዓመት የሥራ ልምድ ያላቸዉ፤ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ውስጥ ለመሳተፍ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር  የተሰጠ ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ የሚችል በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡

  ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር/ አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T 191  በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ  በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡

  ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን በሰም በታሸገ ፖስታ ቴክኒካል ሰነዳቸውን ዋናው እና ቅጁን በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ መጋቢት 25 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ድረስ  ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት የሠራተኞች የመመገቢያ አዳራሽ  ውስጥ በተመሳሳይ ቀን በ 9:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

   ለተጨማሪ ማብራሪያ:- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

   ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

   ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል

  በስልክ ቁጥር 011 517 4028

  ኢ-ሜይል: WoldeM@ethiopianairlines.com  /

  TsegenetF@ethiopianairlines.com

  አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

  የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ