Ethiopian Airlines Group (EAG)

Addis Zemen Tir 22, 2013

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በዝግ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ

ተ.ቁ

የእቃው ዓይነት

መለኪያ

የጨረታ ማስከበሪያ (bid bond)

1

ከአውሮፕላን ላይ የወረደ ነዳጅ ከነበርሜሉ (DEFUELED OIL)

በበርሜል

50,000.00

2

ያገለገሉ መካከለኛ ሻንጣዎች (የሸራ) (Crew Bag Hard Cover)

በቁጥር

10,000.00

3

ያገለገሉ አነስተኛ ሻንጣዎች (የሸራ) (fallow me Canvas Cover)

በቁጥር

10,000.00

4

የፓይለቶች ዶከመንት መያዥያ (የሸራ)(Brief Case)

በቁጥር

10,000.00

5

የሴቶች የእጅ ቦርሳ (Crew hand Bag

በቁጥር

10,000.00

6

የእግር ኳስ ሜዳ ሣር (football field grass)

ባላበት

10,000.00

7

ያገለገለ መካከለኛ ሻንጣዎች (የሸራ)(Normal Bag Canvas Cover)

በቁጥር

 

10,000.00

ማሳሰቢያ፡

 1. ከላይ የተጠቀሱትን እቃዎች የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች Yekatit 9፤ 10 እና 11 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ፡ 3:30 እስከ 6:30 እንዲሁም ከቀኑ 8:30 እስከ 10:30 ሰዓት በእቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ ” በዘርፉ አንድ መቶ (100.00) ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000006958277 (E99 ) የጨረታ ቁጥር (SAT-10/005/13 ) በመጥቀስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ  ( Ethiopian Airlines Group ) ስም ገቢ በማድረግ እና ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ (Deposited slip) በመያዝ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ ማንኛውም ባንከ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ስም የተሰራ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ከላይ በተገለጸው የዋጋዎች ዝርዝር መሰረት በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ማንነታቸውን ከሚገልፅ ያገልግሎ ዘመን ያላለፈ መታወቂያ ጋር ይዘው ቦሌ ዋናው መስሪያ ቤት በመቅረብ የጨረታ ሠነዱን  መግዛት የሚችሉ ሲሆን አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት (CPO) ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል።
 2.  ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ፣ ቲን ነምበር እና ቫት ተመዝጋቢ ወይም የዘመኑን (2012/2013) ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
 3. በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰውን ከአውሮፕላን ላይ የወረደ ነዳጅ (Defueled Oil) ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ወይም ቢሮ አካባቢን በማይበክል መንገድ የሚጠቀሙ መሆኑን የሚገልፅ ደብዳቤና የታደሰ ፈቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
 4. ከተራ ቁጥር 1 እስከ 5 ለተጠቀሰው እቃዎች ተጫራቶች የሁለት ዓመት ኮንትራት ውል መግባት ይኖርባቸዋል፣ ድርጅቱ እቃዎቹ በሚጠራቀሙበት ጊዜ ሲጠሯቸው መጥተው የማንሳት ግዴታ የሚኖርባቸው ሲሆን፣ በተቀመጠላቸው ጊዜ ውስጥ የማያነሱ ከሆነ ግን ድርጅቱ ኮንትራቱን የማቋረጥ መብት አለው።
 5. ከአውሮፕላን ላይ የወረደ ነዳጅ (Defueled Oil) ከነበርሜሉ ስለማይሸጥ አሸናፊዎች (ተጫራቾች) ምትክ በርሜል የማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል።
 6. በተራ ቁጥር 6 እና 7 ላይ የተጠቀሱት እቃዎች ጨረታው የሚከናወነው ለአንድ ጊዜ ብቻ ይሆናል::
 7. ተጫራቾች የእቃዎቹን ያዘት እና ናሙና ሰነዱን በሚገዙበት ወቅት መመልከት ይችላሉ።
 8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋተእታ) (VAT) የማይጨምር ሲሆን፣ የጨረታ አሸናፊዎች ለሚገዙት እቃ ተእታ የመክፈል ግዴታ አለባቸው እንዲሁም ክፍያዎችን ሲፈፅሙ የቲን ቁጥር (TIN No) ማቅረብ አለባቸው።
 9. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ የሚወዳደሩበትን የእቃ ዋጋ በሚነበብ ሁኔታከሞሉ በኋላ በፖስታ (Envelope) በማሸግ እና የሚወዳደሩበትን የእቃ እይነት እንዲሁም የራሳቸውን ሙሉ ስም በፖስታ (Envelope) ላይ በመጻፍ Yekatit 12 ቀን 2013 ዓ.ም ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት መግቢያ በር ላይ እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
 10. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት- Yekatit 13 ቀን 2013 ዓ.ም ከረፋዱ 4:30 ሰዓት ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይሆናል::
 11. ከላይ የተጠቀሱትን እቃዎች ያሸነፉ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ሙሉ ዋጋ በቅድሚያ በመከፈል እቃዎቹን ካሸነፉበት ቀን ጀምሮ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ይህ ባይሆን ግን ድርጅቱ ጨረታውን የሚሰርዝ መሆኑን እና ለጨረታው ያስያዙትንም ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ የሚሆን መሆኑን ያሳውቃል::
 12. በትክክል የማይነበብ እና ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ እንዲሁም ያልታሸገ ፖስታ ተቀባይነት የለውም::
 13. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ እና ሰነድ ለመግዛት እነዚህን ኢሜል ወይም ስልክ ቁጥር መጠቀም ይችላሉ::

NIGUSSIEA@ethiopianairports.com   Birhans@ethiopianairlines.com  

ስልክ ቁጥር፡-251-11-5-7-4118 ፣ስልክ ቁጥር፡-251-11-5-178781

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ