Ethiopian Broadcast Authority

Addis Zemen Tir 8, 2013

የንግድ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ ለመስጠት

 የወጣ  የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን በብሮድካስት አገልግሎት አዋጅ ቁጥር 533/99 አንቀጽ 7(2) በተሰጠው ሥልጣንና ተግባር መሠረት በሁሉም ክልሎች በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች የንግድ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያ ለማቋቋም የሚፈልጉ አመልካቾችን አወዳድሮ የሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ መስጠት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት፡

  •  በአዲስ አበባ ከተማ ለሚሠራጭ የንግድ ኤፍ ኤም የሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት 89.1 91.1 95.5 99.8 እና 103.5 ሜጋ ሄርዝ (MHz)
  • በድሬዳዋ ከተማ ለሚሠራጭ የንግድ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት 90.9 ሜጋ ሄርዝ (MHZ)
  • በአዳማ ከተማ ለሚሠራጭየንግድ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት 107.1 ሜጋ ሄርዝ (MHz)
  • በጅማ ከተማ ለሚሰራጭ የንግድ ኤፍኤም ሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት 101.0 ሜጋ ሄርዝ (MEZ)
  • በሐዋሳ ከተማ ለሚሠራጭ የንግድ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት 104.8 ሜጋ ሄርዝ MHz
  • ባሕርዳር ከተማ ለሚሠራጭ የንግድ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት 98.5 እና 88.9 ሜጋ ሄርዝ (MHZ)
  • በሐረር ከተማ ለሚሠራጭ የንግድ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት 99.4 ሜጋ ሄርዝ (MHz)
  • በጅግጅጋ ከተማ ለሚሠራጭ የንግድ ኤፍ ኤም ራዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት 92.9 106.5 ሜጋ ሄርዝ (MEZ)
  • በአሶሳ ከተማ ለሚሠራጭ የንግድ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት 94.6 ሜጋ ሄርዝ (MHZ)
  • በጋምቤላ ከተማ ለሚሠራጭ የንግድ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ብሮድካስት አገልግሎት 90.8 ሜጋ ሄርዝ (MEZ) በአጠቃላይ 14 የሬዲዮ ሞገዶችን ዝግጁ አድርጎ አመልካቶችን በማወዳደር ፈቃድ መስጠት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከላይ በተጠቀሱት ከተሞች የንግድ ኤፍ ኤም ብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ ለማግኘት መወዳደር የምትፈልጉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 (ሰላሣ) ተከታታይ ቀናት ከኤግዚቢሽን ማዕከል ጀርባ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 601 ብር 50 (ሃምሣ ብር) በመክፈል የማመልከቻ ቅጽ ወስዶ በመሙላት እና ለውድድሩ አስፈላጊ የሆነ ሠነዶችን ከማመልከቻ ቅጹ ጋር በማያያዝ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የጨረታ ሣጥኑ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በታተመ 31ኛው ዕለት በባለሥልጣኑ የመሠብሰቢያ አዳራሽ ከቀኑ 400 ሰዓት ተዘግቶ 430 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115-53-87-65 /66/60/ 011553-87-55/56 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ሥልጣን