Ethiopian Broadcast Authority

Addis Zemen Tahsas 25, 2013

በድጋሚ የወጣ የስራ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ከሴቶች ሕጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በሕፃናት ላይ የሚሰሩ የራዲዮ እና የቴሌቭዥን ፕሮግራሞች ደረጃቸውን በጠበቀና ወጥ በሆነ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ የሚያስችል የአሠራር  ሥርዓት ለመዘርጋት በሐገር አቀፍ ደረጃ ጥናት ለማስጠናት ይህን የሥራ ጨረታ አዘጋጅቷል። ይህ የሥራ ጨረታ ማስታወቂያም በዘርፉ የተለያዩ የጥናት ሠነዶችን ያዘጋጀና ብቃት ያላቸው ድርጅቶች በሕጻናት ሁለንተናዊ ዕድገትና ጥበቃ (Child Development & Protection) ላይ እንዲሁም የቤተሰብ ክህሉትና እውቀት፣ ሕጻናትን በተመለከተ በብዙኃን መገናኛዎች የሚተላለፉ ፕሮግራሞች ይዘት (Content) መጠንና ሽፋን በልዩ ጥንቃቄና ትኩረት ወጥነት ባለው መልኩ የጥናት ጽሁፎች ላይ የተሠማሩ ድርጅቶችን በይፋ አወዳድሮ ለመቅጠር የወጣ ነው።ዓላማ፤

  • የሕፃናትን ጉዳይ በሁሉም የራዲዮ እና የቴሌቭዥን አውታሮች የቅድሚያ አጀንዳ ሆኖ ትርጉም ባለው መልኩ የሚተገበርበትን አሠራር በመዘርጋት ሁለንተናዊ ደህንነቱ የተጠበቀ መልካም ትውልድ ማፍራትና ጥቅም ላይ የሚውሉ የሚዲያ መልክቶች ይዘት ለሚከተሉት ጉዳዮች ትከረትና አጽዕኖት በሰጠ አግባብ ማጋጀት ይጠበቅባቸዋል።
  • በሕፃናት ሁለንተናዊ ዕድገት የግንባታ ሂደት የብዙሀን መገናኛዎችን ሚና ማሣደግ።
  • ሕፃናትን በተመለከተ በብዙሀን መገናኛዎች የሚተላለፉ ጉዳዮች ይዘት ማሻሻል።
  •  ሁሉም የብዙሀን መገናኛዎች በትወልድ ግንባታ ሂደት የሚመሩበትን አሠራር መዘርጋት።
  • ተወዳዳሪ ድርጅቶች ማሟላት /ማቅረብ የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች/ ጉዳዮች፤
  • ምክረሃሳባቸውን በአማርኛ ወይም በእንግሊዝኛ ቋንቋ  አዘጋጅተው ማቅረብ ይችላሉ። ስለሚያዘጋጁት ሠነድ መቼ፣ እንዴት፣ በማን እንደሚተገብሩት ከሚገልጽ የድርጊት መርሃ ግብር እና ሥራውን በምን ያህል ገንዘብ እንደሚያከናውኑት  ከሚገልፅ የዋጋ መግለጫ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  • የድርጊት መርሃግብሩ እና የዋጋ መግለጫውን በተለያየ ፖስታ አሽገው ማስረከብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን፤ በአንድ ፖስታ ታሽገው የሚቀርቡ መወዳደሪያ የቴክኒክ ምክረሃሳብ እና  የዋጋ መግለጫ ሠነዶች ከውድድር ውጪ ይደረጋሉ፡፡
  • ተወዳዳሪዎች የታደሠ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ፣ የተጨማሪ  እሴት ታክስ እና ቲን ቁጥር ምዝገባ፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማሥረጃ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
  • CPO/Cash Payment order / 10,000 ብር አያይዘው ማቅረ አለባቸው። በተጨማሪም የአቅራቢነት ምዝገባ ቢቀርብ የተሻለ ነው። በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎቱ ያላቸው በዘርፉ የተሠማሩ ድርጅቶች ምክረሃሳባቸውን እና የዋጋ መግለጫ ሠነዳቸውን ይህ የሥራ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ ባለሥልጣኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት  መሣተፍ ይችላሉ። ባለሥልጣኑ የሥራ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።የጨረታ ሠነድ መግዣ ዋጋ 100.00 ብር ሲሆን፤ ተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ በስልክ ቀጥር 0912085683 ወይም 0912492984 0115573362 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።

አድራሻ፡አዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኦሎምፒያ ከኤግዚቢሽን ማዕከል ጀርባ

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን