Ethiopian Statistical Association(ESA)

Addis Zemen Tir 29, 2013

የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ባለሙያዎች ማኅበር በኢፌዴሪ የፍትሕ ሚኒስቴር የበጎ አድራጎትና ማኅበራት ኤጀንሲ የተመዘገበ የሙያ ማኅበር ነው፡፡ ማኅበሩ 2020 የሒሳብ እንቅስቃሴውን ለማስመርመር የውጭ ኦዲተሮችን ማወዳደር ይፈልጋል።

ስለሆነም የማኅበሩ 2020 የሒሳብ መዝገብ ከሁለት ቦክስ ፋይል እና የባንክ ሒሳቡም ከብር 1,899,927,20 (አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀያ ሰባት ብር ከሀያ ሣንቲም) ሲሆን፤ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ሕጋዊ እና የሚከተለውን መሥፈርት ማሟላት የሚችል ኦዲተር የማይመለስ ሙሉ ማሥረጃውን ፎቶ ኮፒ እና የዋጋ ዝርዝር እንዲሁም ሥራውን ሠርቶ የሚያስረክብበትን የጊዜ ገደብ በመጥቀስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በማህበሩ /ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት እንድታስገቡ ይጋብዛል፡፡

ማሳሰቢያ፡ለውድድር የሚቀርበው ኦዲተር የሚከተሉትን መሥፈርቶች በግልፅ ማመላከት አለበት፡፡

. የሙያ ማረጋገጫ ያለው፣

ለ. የንግድ ፈቃድ ያለው፣

ሐ.የዘመኑን ግብር ስለመክፈሉ መረጃ ማቅረብ የሚችል፣

. የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር ያለው፣

. ከፊዴራል ወይም ክልል ኦዲተር መሥሪያ ቤት ለበጀት ዓመቱ የታደሠ ፈቃድ ያለው፣ ማኅበሩ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የተፈጥሮ ሣይንስ ኮሌጅ፣

የሥነምድር ጥናት ሕንጻ፣ ቢሮ ቁጥር 216

ስልክ፡– 0111261203/ 0930364273

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ባለሙያዎች ማኅበር