Addis Ababa City Administration Police Commission

Addis Zemen ጳጉሜ3፣2012

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር AAPC NCB002/2012 ዓ.ም 

የአ/አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን 2013 በጀት ዓመት ለኮሚሽኑ የተለያዩ የሥራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ጨረታዎችን በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ሎት

የጨረታ ዓይነት 

ናሙና በተመለከተ 

የጨረታ ማስከበሪያ 

001

የተለያዩ አይነት የስፖርተኞች ትጥቅ ማለትም የእግር ኳስ የመረብ ኳስ የቦክስ አትሌቲክስና 

የብስክሌት ተወዳዳሪዎች ቡድን ሙሉ ትጥቅና የውድድር ብስክሌት የመለዋወጫ ዕቃዎች 

ከኮሚሽኑ ፍላጎት(ስፔስፊኬሽን) መሰረት ናሙና የሚቀርብበት 

50,000

002

የማርቺንግ ባንድ የሴትና የወንድ የደንብ ልብስ /ዩኒፎርም/ እና ጫማዎች 

በኮሚሽኑ ፍላጎት (ስፔስፊኬሽን) መሰረት ናሙና የሚቀርብበት 

30,000

003

የአስክሬን መጠቅለያ ፕላስቲክ 

በኮሚሽኑ ፍላጎት (ስፔስፊኬሽን) መሰረት ናሙና የሚቀርብበት 

10,000

004

የተለያዩ የሚዲያና የስቱዲዮ ሥራ የሚያገለግሉ ዕቃዎች 

ኮሚሽኑ ባዘጋጀው ስፔስፊኬሽን መሠረት 

100,000

005

ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ የእጅ የመገናኛ ሬዲዮኖች እና የተለያዩ የሬዲዮን መለዋወጫ

ኮሚሽኑ ባዘጋጀው ስፔስፊኬሽን መሠረት 

300,000

ስለዚህ:- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው። 

 1. በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን እና በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው ይመልከቱ የሚል ፅሁፍ በግልጽ ማቅረብ አለባቸው።
 2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፡፡ 
 3. ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡ 
 4. የታደለ የዘመኑን ንግድፍቃድ እና የታደሠ ንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው። 
 5. የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው::
 6. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 7. አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም፡፡
 8. በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ 
 9. ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን /ፋይናንሻል/ሰነዶች በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለባቸው፡፡ 
 10. ማንኛውም ተጫራች የሚያስገባው ሰነድ ፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር የሚጫረትበትን ዕቃ አይነት በትከክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ ማህተም በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን ፤ ስርዝ ድልዝ ስፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ 
 11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያሲዙት ሲፒኦ ከቴክኒክ ሰነዶችጋር በአንድ ላይ ታሽገው መቅረብ አለባቸው። 
 12. በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን ወይም አገልግሎቱን በራሳቸው ትራንስፖርት አ/አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት ግምጃ ቤት ወይም በክፍል 6 በፍላጎት ሙግለጫው በተጠቀሰው የማስረከቢያ ቦታ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው።
 13. በጨረታ ሰነድ በክፍል 6 ውስጥ በሚገኘው የፍላጎት መግለጫ ላይ በሚገለፀው መሰረት ጨረታ ሰነዱ ላይ በቀረበው መሰረት ናሙና ማቅረብ አለበት :: 
 14. ተጫራቾች ያቀረቡት ናሙናም ሆነ አሸናፊ መሆናቸው ሲረጋገጥ ያቀረቡአቸው ዕቃዎች ኮሚሽኑ ባወጣው ፍላጎት መግለጫ /specification/ መሰረት መሆኑን በኮሚሽኑ የጥራት ኮሚቴ ወይም በኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ኤጀንሲ አማካኝነት የሚረጋገጥ ይሆናል። 
 15. ናሙናው ገቢ መሆን ያለበት ጨረታው ከሚከፈትበት ከአንድ ቀን በፊት መሆን አለበት። 
 16. ተጫራቾች አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ ግዢ ጽ/ቤት ቢሮቅርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፣ 
 17.  ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በማግስቱ በ 16ኛው ቀን እስከ ከሰዓት 7፡30 ሠዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ በኮሚሽኑ ግዢና ፋይናንስ 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። 
 18. በጨረታ ሰነዱ ክፍል 2 ላይ በሚጠቀሰው ቀን ጠዋት4፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 5፡00 ሰዓት ሲሆን ፤በመ/ቤቱ 5ኛ ፎቅ ትንሹ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 512 ይከፈታል። 
 19. የጨረታው መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው 4፡30 ሰዓት ታሽጎ 5፡00 ሰዓት ሲሆን ይከፈታል፡፡ 
 20. . ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ 

-መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ስሰክ ቁጥር 0118625800 

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን